Revised Urban and Rural Potable Water Supply and Sewerage Services’ Reorganizing Proclamation Implementation, Council of Regional Government Regulation (No. 94/2012)
颁布于 2012-05-18 · 文本截至 2026-10-01
以研究形式发布的公开法律与官方指引,不构成法律、税务或金融建议。
研究内容本身以英文撰写。标题和标签已翻译,调查结果和引文未翻译。
关于这部法律
- 语言
- English
- 类型
- 条例
- 国家
- 埃塞俄比亚 · Amhara
- 主题
- Water
- 关键词
- water supply, sewerage, waterworks, freshwater pollution, institution, offences/penalties, pollution control, governance
在哪里阅读
该法律没有记录来源链接。
文本
所收录的法律原文,按条款排列。每个条款都有自己的链接。
ገጽ-1- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -1 በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዝክረ-ሕግ ZIKRE-HIG OF THE COUNCIL OF THE AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE IN THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA ማውጫ ደንብ ቁጥር 94/2004 ዓ.ም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የከተማና ገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች እንደገና ማደራጃ አዋጅ ማስፈፀሚያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ Contents Regulation No. 94/2012 The Revised Amhara National Regional State Urban and Rural Potable Water Supply and Sewerage Services’ Reorganizing Proclamation Implementation, Council of Regional Government Regulation. ደንብ ቁጥር 94/2004 ዓ.ም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የከተማና ገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶችን እንደገና ለማደራጀት የወጣውን አዋጅ ለማስፈፀም የወጣ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ REGULATION NO. 94 /2012 A COUNCIL OF THE REGIONAL GOVERNMENT REGULATION ISSUED TO PROVIDE FOR THE IMPLEMENTATION OF THE REVISED URBAN AND RURAL POTABLE WATER SUPPLY AND SEWERAGE SERVICES REORGANIZING PROCLAMATION IN THE AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE የአንዱ ዋጋ ብር Price Birr 15.34 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ISSUED UNDER THE AUSPICES OF THE COUNCIL OF THE AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE የ ፖ.ሣ.ቁ 312 P.o. Box ባህር ዳር ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Bahir Dar 18 th , May 2012 17ኛ አመት ቁጥር 9 17 th Year No 9 16 th Year No 15 www.abyssinialaw.com ገጽ-2- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -2 በክልሉ ውስጥ እያደገ የመጣውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የፍሳሽ አወጋገድ አስተማማኝ ለማድረግ ይቻል ዘንድ የአገልግሎት መስጫ ተቋማቱን እንደገና ለማደራጀት አዋጅ ቁጥር 188/2003 ዓ.ም ተሻሽሎ የወጣ በመሆኑ፤ WHEREAS, with a view to making the ever increasing potable water supply and sewerage disposal service in the regional state reliable, the revised Proclamation No 188/2011 reorganizing the service providing institutions has been so enacted; ከመሠረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ ጥናት ግኝት አንፃር የማስፈጸሚያ ደንቡን አተገባበር ለየተቋማቱ የተቀላጠፈና ውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥ አመች እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤ WHEREAS, it has become appropriate to make the implementation of the executionary regulation convenient for the expedient and effective service provision by each institutions having due regard to the findings of the Basic Business Process Reengineering thereof; የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተሻሻለው የብሄራዊ ክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 7 እና ተሻሽሎ በወጣው የከተማና ገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች እንደገና ማደራጃ አዋጅ ቁጥር 188/2003 ዓ.ም አንቀጽ 26 ድንጋጌ ሥር በተሠጠው ስልጣን መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡ NOW, THEREFORE, the Council of the Amhara Regional Government, pursuant to the powers vested in it under the provisions of Art. 58 Sub Art. /7/ of the Revised Constitution of the National Regional State and Art. 26 of the revised Urban and Rural Potable Water Supply and Sewerage Services Reorganization Proclamation No. 188/2011, hereby issues this regulation as follows. ክፍል አንድ PART ONE ጠቅላላ GENERAL 1. አጭር ርዕስ 1. Short Title ይህ ደንብ “የተሻሻለው የከተማና ገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች እንደገና ማደራጃ አዋጅ ማስፈፀሚያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 94/2004 ዓ.ም.” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ This regulation may be cited as “the Revised Urban and Rural Potable Water Supply and Sewerage Services’ Reorganizing Proclamation Implementation, Council of Regional Government Regulation No. 94/2012”. www.abyssinialaw.com ገጽ-3- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -3 2. ትርጓሜ 2. Definitions የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡ Unless the context requires otherwise, in this regulation: 1. “አዋጅ” ማለት ተሻሽሎ የወጣዉ የከተማና ገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች እንደገና ማደራጃ አዋጅ ቁጥር 188/2003 ዓ.ም ነው፤ 1. “Proclamation” shall mean the Revised Urban and Rural Potable Water Supply and Sewerage Services’ Reorganization Proclamation No. 188/2011; 2. “ቢሮ” ማለት በአዋጁ አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 3 ስር የተመለከተው አካል ነው፤ 2. “Bureau” shall mean the body indicated under Art. 2 Sub Art. 3 of the Proclamation; 3. "ደምበኛ” ማለት በዚህ ደንብ መሠረት ከከተማ ወይም ከገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የንፁህ መጠጥ ውሃ ወይም የሳኒቴሽን አገልግሎት የሚያገኝ ማንኛውም ሰው ነው፡፡ 3. “Customer” shall mean any person who obtains potable water supply or sanitary services from Urban or Rural Potable Water Supply and Sewerage Services pursuant to this Regulation; 4. “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤ 4. “Person” shall mean any natural or juridical person; 5. “የስራ መሪ” ማለት በአዋጁ፣ በዚህ ደንብ፣ ወደፊት በሚወጡት የስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንቦችና ልዩ ልዩ መመሪያዎች መሰረት የተሰጡትን ወይም የሚሰጡትን ስልጣንና ተግባራት እንዲያከናውን በቦርድ የተቀጠረን ስራ አስኪያጅና በስሩ የሚገኙትን ሌሎች ስራ መሪዎች ያካትታል፤ 5. “Manager” shall include a manager recruited by the board and other managers subordinate to him in order to carry out the powers and functions entrusted or to be entrusted to him by the Proclamation, this Regulation, managerial bylaws and various directives which may be issued subsequently; 6. “ጽ/ቤት” ማለት የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ነው፤ 6. “Office” shall mean the Office of Urban Potable Water Supply and Sewerage Service; 7. “አገልግሎት” ማለት ለተጠቃሚው ኅ/ሰብ የሚቀርብ ማናቸውም ዓይነት የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ነው፤ 7. “Service” shall mean any kind of potable water supply and sewerage service provided for the user community; 8. "የፍሳሽ መስመር" ማለት የተለያዩ የፍሳሽ መስመሮችንና በፍሳሽ መስመሮች ላይ የሚኖሩ የፍተሻ ቀዳዳዎችን የሚጨምር ይሆናል፤ 8. “Sewage Pipeline” shall include those various sewage pipelines as well as check holes existing in the Sewage Pipelines; www.abyssinialaw.com ገጽ-4- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -4 9. “የአገልግሎት ክፍያ” ማለት ደንበኞች የውሃና ፍሳሽ መስመሮችን ሲያዘረጉ፣ ሲያዛውሩ፣ ቆጣሪ ሲያስመረምሩ፣ ሲያስጠግኑ ወይም ለስራው የሚያስፈልገውን ንብረትና ገንዘብ ሲያስገምቱ የሚፈጽሙት ክፍያ ነው፤ 9. “Service Charge” shall mean payment made by customers where they cause the installation, relocation, water meter testing, maintenance of water supply and sewage lines as well as the cost estimation of such materials and money as may be required for the work; 10. “መስመር መለወጥ” ማለት አስቀድሞ የተዘረጋን የውኃ ወይም የፍሳሽ መስመር ስፋቱ ሳይለወጥ የቧንቧውን ዓይነት በመቀየር ብቻ መልሶ መዘርጋት ነው ፡፡ 10. “Line Alteration” shall mean reinstalling previously installed water or sewer pipeline by merely changing the pipe type without altering its size; 11. ”መስመር ማሻሻል” ማለት በጽ/ቤቱ ወይም በደንበኛው ወይም በሌላ በማናቸዉም ሰው አነሳሽነት አስቀድሞ የተዘረጋን የውኃ ወይም የፍሳሽ መስመር መጠኑን በመጨመር ወይም በመቀነስ በዚያው ስፍራ መልሶ መዘርጋት ነው፤ 11. “Line Improvement” shall mean reinstalling previously installed water or sewer pipeline in the same place by maximizing or minimizing its size with the initiation of the office or customer or any other person; 12. "መስመር ማዛወር" ማለት በጽ/ቤቱ ወይም በደንበኛው ወይም በሌላ በማናቸዉም ሰው አነሳሽነት አስቀድሞ የተዘረጋን የውኃ ወይም የፍሳሽ መስመር ከአንዱ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ የመስመሩን ስፋት እንዳለ በመጠበቅ ወይም በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዛወር ነው፤ 12. “Line Relocation” shall mean relocating previously installed water or sewer pipeline from one place to the other by keeping the size of the pipeline as its stand or by maximizing or minimizing same with the initiation of the office or a customer or any other person; 13. "ቆጣሪ" ማለት ጽ/ቤቱ ለደንበኛው የሚያቀርበውን የውኃ መጠን ለመለካት የሚያገለግል መሳሪያ ነው፤ 13. “Water-meter” shall mean an instrument which is used to measure the volume of water that the office provides to the customer; 14. "የመኖሪያ ቤት ያልሆነ ደንበኛ" ማለት ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ ተቋም፣ ንግድ ቤት፣ የምርት ማእከል፣ የመንግስት መ/ቤት፣ መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የመዝናኛ ቦታ ወይም ለሌላ ልዩ ልዩ ጠቀሜታ የሚውል 14. “Non Residential Customer” shall mean any person who inters into contract with the office in order to acquire a water service to be utilized for an institution, business establishment, production center, public office, governmental or nongovernmental service providing institutions, www.abyssinialaw.com ገጽ-5- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -5 የውኃ አገልግሎት ለማግኘት ከጽ/ቤቱ ጋር የተዋዋለ ማንኛውም ሰው ነው፤ recreational places or for various uses other than residence; 15. "የመኖሪያ ቤት ደንበኛ" ማለት ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል የውኃ አቅርቦት አገልግሎት ለማግኘት ከጽ/ቤቱ ጋር የተዋዋለ ማንኛውም ሰው ነው፤ 15. “Residential Customer” shall mean any person who inters into contract with the office in order to acquire a water supply service for residential use; 16. "ከቆጣሪ በፊት" ማለት ከጽ/ቤቱ አነስተኛ መስመር ጀምሮ በደንበኛው ቤት ህንጻ ወይም ግቢ እስከሚገኘው ቆጣሪ ድረስ ያለው መስመር ነው፡፡ 16. “Pre-Water Meter” shall mean that pipeline starting from the medium pipeline of the office up to the water meter located in the home building or premises of the customer; 17. "የውኃ ማደያ" ማለት በመስተዳድር አካል ወይም በሌላ በማናቸውም ሕጋዊ አካል ተዋዋይነት፣ አስተዳደርና ወይም ቁጥጥር ስር ሆኖ በግል ውኃ ማስገባት ለማይችሉ የሕ/ሰብ ክፍሎች የጋራ መጠቀሚያ እንዲውል የተተከለ የውኃ ማከፋፈያ ቦታ ነው ፡፡ 17. “Public Fountain” shall mean a water distribution place contractually held, administered and/or controlled under a governmental organ or any other legal body, having been installed for the common use of those community groups who are not capable to acquire water on an individual basis; 18. "የውኃ መስመር" ማለት ንጹህ ውኃ ለማስተላለፍ የተዘረጋ ማናቸውም ቧንቧ ነው፡፡ 18. “Water Line” shall mean any pipeline installed to convey clean water. 3. ዓላማዎች 3. Objectives ደንቡ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡- The regulation shall have the following objectives: 1. በአዋጁ ውስጥ የተመለከቱትን የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ደንበኞች መብቶችና ግዴታዎች በተሟላ ሁኔታ ማስከበርና የተጠቃሚውን ህብረተሰብ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ 1. To fully enforce the rights and obligations of those customers of water and sewerage service specified in the Proclamation and thereby create a suitable condition enabling to increase production and productivity on the part of the user community; 2. የውሃ አጠቃቀም ስርዓቱ ከብክነት የተጠበቀና ከብክለት የጸዳ እንዲሆን ማድረግ፣ 2. To cause the water utilization system be protected from wastage and get free from pollution thereof; www.abyssinialaw.com ገጽ-6- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -6 3. በሀገሪቱ የውሃ ሃብት አስተዳደር ፖሊሲና በአዋጁ ድንጋጌዎች መሰረት በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች የኢንቨስትመንት፣ የኦፕሬሽንና የጥገና ወጭዎችን በሚያስመልስ መልኩ ተደራጅተው ሊሰሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ 3. To facilitate the situation enabling the potable water supply and sewerage services of the region to organize and operate in such a way as to make them become capable of recovering the investment, operation and maintenance costs in accordance with the country’s Water Resource Management Policy and the Proclamation; 4. የያንዳንዱን ደንበኛ የውሃ አጠቃቀምና የአጠቃቀሙን አጠቃላይ ባህርይ ያካተተ የመረጃ ስልት በመንደፍ በክልሉ ውስጥ ሰፊ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋንና የፍሳሽ አወጋወገድ ስርአት በመዘርጋት በውሃው ዘርፍ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግብ ማሳካት፣ 4. to achieve the millennium development goal in the water sector by putting in place a wider coverage of potable water supply and sewerage disposal system as well as by designing an information mechanism encompassing the water utilization of each and every water customer and the general nature of utilization thereof; 5. መላው ህብረተሰብ በውሃ ተቋማት ግንባታና አስተዳደር ውስጥ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት በማድረግ ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የውሃ አጠቃቀም ስርአት እንዲዘረጋ ማስቻል፣ 5. To enable the general community install a fair, expedient and effective water utilization system which would assist it play its own role in the construction and administration of the water supply facilities; 6. በየአካባቢው በሚቋቋሙት የውሃ ስራ አመራር ቦርዶች ውስጥ የሴቶችን ተዋጽኦ ለይቶ በማመልከት ለመልካም አስተዳደር ስርአት መስፈን ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት፡፡ 6. To provide a formidable contribution for the prevalence of good governance by duly identifying and specifying the composition of women in the boards of water management to be established in each and every area; www.abyssinialaw.com ገጽ-7- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -7 ክፍል ሁለት PART TWO ስለከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ደረጃ አሰጣጥና ስለ ስራ አመራር ቦርዶች GRADING OF URBAN POTABLE WATER SUPPLY AND SEWERAGE SERVICES AND THE BOARDS OF MANAGEMENT 4. የውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶችን ደረጃ ለመወሰን የሚያስችሉ ዝርዝር መስፈርቶች 4. Specific Criteria Enabling to Determine the Grading of Water Supply and Sewerage Services 1. የአዋጁ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ዝርዝር መስፈርቶች መሠረት በማድረግ በደረጃ ይመደባሉ፡ 1. Without prejudice to the provision of Art. 7 Sub Art. /1/ of the Proclamation, the Urban Potable Water Supply and Sewerage Services existing in the Region shall be categorized on the basis of the specific criteria indicated here below: ሀ/ የውኃ ተጠቃሚ ደንበኛ ብዛት --------20% a. Number of water supply customers …… …………………………………..…… 20% ለ/ የሚሰበሰበው ዓመታዊ ገቢና ከመደበኛ ወጪ በተጨማሪ ለማስፋፊያ እና ለሪሃብሊቴሽን የወጣ ወጪ መጠን 30% b. Income to be collected per annum as well as the amount of expense deployed for the expansion and rehabilitation beyond current expenditures……………………....…..30% ሐ/ የከተማውን ነዋሪዎች ሙሉ ፍላጎት የሚያረካ አስተማማኝ የውኃ አቅርቦት መኖር ---------------------------------15% c. Existence of a reliable water supply capable of fully satisfying the needs of the urban dwellers ………………….……...…..15% መ/ የኢንቨስትመንት ወጪን የመመለስ ብቃት ---------------------------------15% d. Capacity to recover the investment cost ……………………….……………..….15% ሠ/ ለመጠባበቂያ የሚሆን በባንክ ያለ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ----------10% e. Amount of money deposited in the bank for contingency purposes…………….…..10% ረ/ የከተማው ፖለቲካዊና ኢኮኖያዊ ፋይዳ 5% f. The political and economic significance of the urban center……………………… 5% www.abyssinialaw.com ገጽ-8- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -8 ሰ/ በ 5 ዓመት ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 1 ጊዜ የሚደረግ የታሪፍ መሻሻል -----------5% g. A revision of tariff to be undertaken at least once in the period of 5 years …………..5% 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የሰፈሩት መመዘኛዎች ዝርዝር አፈጻጸም ቢሮው ወደፊት በሚያወጣው መመሪያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡ 2. The specific implementation of the criteria stipulated under Sub Art. 1 of this Article hereof shall be elaborated in a subsequent directive to be issued by the Bureau. 5. ደረጃዎችን ስለመወሰን 5. Determination of Grades 1. በዚህ ደንብ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር በተመለከቱት መስፈርቶች አጠቃላይ ድምር ውጤት መሠረት በክልሉ ከተሞች የሚገኙት የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ደረጃ ከዚህ በታች በተመከተው አኳኋን ይወሰናል፡ 1. The grading of Potable Water Supply and Sewerage Services located in the urban centers of the Regional State shall, on the basis of the total result of the criteria specified under Art. 4 Sub Art. 1 of this Regulation hereof, be determined as follows: ሀ/ ውጤቱ ከ90% እስከ 95% የሆነ ----- 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፤ a. One whose result is 90% through 95% ----- 1 st grade Potable Water Supply and Sewerage Service; ለ/ ውጤቱ ከ75% እስከ 89% የሆነ ------ 2ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፤ b. One whose result is 75% through 89% ----- 2 nd grade Potable Water Supply and Sewerage Service; ሐ/ ውጤቱ ከ60% እስከ 74% የሆነ ------ 3ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፤ c. One whose result is 60% through 74% ----- 3 rd grade Potable Water Supply and Sewerage Service; መ/ ውጤቱ ከ45% እስከ 59% የሆነ ------ 4ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፤ d. One whose result is 45% through 59% ----- 4 th grade Potable Water Supply and Sewerage Service; ሠ/ ውጤቱ ከ30% እስከ 44% የሆነ ------ 5ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፤ እና፣ e. One whose result is 30% through 44% ----- 5 th grade Potable Water Supply and Sewerage Service; and, ረ/ ውጤቱ ከ20% እስከ 29% የሆነ ------ 6ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፤ f. One whose result is 20% through 29% ----- 6 th grade Potable Water Supply and Sewerage Service. www.abyssinialaw.com ገጽ-9- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -9 2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ውጤቱ ከ95% በላይ የሆነ ውሃ አገልግሎት በአዋጁ አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀጽ 10 መሰረት ወደ ባለስልጣን ደረጃ እንዲሸጋገር ቢሮው የውሳኔ ሀሳቡን ለክልሉ መስተዳድር ም/ቤት የሚያቀርብ ሲሆን ውጤቱ ከ20% በታች ሆነ ማናቸውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ደግሞ በኮሚቴ ደረጃ የሚመራ ይሆናል፡፡ 2. Without prejudice to Sub Art. 1 of this Article hereof, the bureau shall submit its recommendation to the Council of Regional Government as regards a water service whose result exceeds 95% so as to transform same to the level of the authority pursuant to Art. 25 Sub Art. 10 of the Proclamation; provided, however, that any Potable Water Supply and Sewerage Service whose result is below 20% shall be managed by and under a committee basis. 3. ቢሮው በዚህ ደንብ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የተመለከቱትን መስፈርቶች እና እያንዳንዱ አገልግሎት ያገኘውን የመለኪያዎች አጠቃላይ መቶኛ ክብደት ደረጃ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ከሶስት እስከ አምስት አመት ባለው ጊዜ ውስጥ እያጠና በሚደርስበት ግኝት መሠረት የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶችን ደረጃ ከፍ ወይም ዝቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡ 3. The bureau may either upgrade or downgrade the Potable Water Supply and Sewerage Services in accordance with the findings available upon studies to be conducted within 3 through 5 years as of the time of grading depending on the criteria indicated under Art.4 Sub Art. 1 of this Regulation hereof and the points each service has scored out of the total weight of the measurements expressed in percentage. 6. መረጃ ስለመስጠት 6. Provision of Information 1. የያንዳንዱ የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለደረጃ አወሳሰን የሚረዱ ትክክለኛ መረጃዎችን ከደጋፊ ሰነዶች ጋር በየአመቱ ለቢሮው ያቀርባል፡፡ 1. The office of every Urban Potable Water Supply and Sewerage Service shall annually submit to the Bureau any accurate information with supportive documents helpful for the determination of grading thereof. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የተጠቀሰውን መረጃ በወቅቱ ያላቀረበ ወይም የተጋነነ መረጃ ያቀረበ የትኛውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በቢሮው በሚሰጠው የደረጃ ማሻሻያ ውሳኔ ተጠቃሚ አይሆንም፡፡ 2. Each and every office of the Potable Water Supply and Sewerage Service failing to timely submit the information stipulated under sub Art.1 of this Article hereof or has otherwise submitted exaggerated information may not enjoy the benefits emanating from the grade determining decision to be granted by the Bureau. www.abyssinialaw.com ገጽ-10- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -10 7. ስለሥራ አመራር ቦርድ አመሰራረት፣ ስለአባላት ተዋጽኦ እና ቁጥር አወሳሰን 7. Establishment of the Board of Management, Composition of Membership and Determination of their Number 1. በአዋጁ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ /1/ እና አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ /2/ ድንጋጌዎች መሰረት በከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤቶች አደረጃጀት ውስጥ የሚቋቋመው የስራ አመራር ቦርድ እንደ አስፈላጊነቱ ቁጥራቸው ከ 5 እስከ 7 የሚደርሱ አባላት የሚኖሩት ሲሆን፣ የአባላቱ ስብጥር እንደሚከተለው ይሆናል፡ 1. The Management Board to be established within the organization of the Office of Urban Potable Water Supply and Sewerage Services shall, pursuant to the provisions of Art.8 Sub-Art. /1/ and Art.9 sub-Art. /2/ of the Proclamation, as deemed necessary, comprise 5 through 7 members, whose composition is listed as follows: ሀ/ ከክልሉ መንግስት ተቋማት ቢያንስ 2 ሴቶች የሚገባቸው 4 ሰዎች -------አባላት፣ a. Four persons to be drawn from the Regional Government institutions, (out of whom the two are women), ………….……..members; ለ/ ከመካከላቸው አንዷ ሴት መሆኗ እንደተጠበቀ ሆኖ ከውሃ ተጠቃሚው ሕብረተሰብ ተመርጠው የሚሰየሙ 2 ተወካዮች ---------------አባላት፣ b. Two representatives selected from among the water-user community, (with one of them being woman), …………………..members; ሐ/ ከንግዱ ማህበረሰብ የሚወከል 1 ሰው አባል፣ c. A person to be represented from the business community…………..…….......…..member; መ/ የውሃ አገልግሎቱ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ድምፅ አልባ ፀሀፊ፡፡ d. The manager of the water service office ………………………non-voting secretary; 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ከፊደል ተራ ቁጥር ሀ - ሐ የተጠቀሱት የቦርዱ ሰብሳቢና አባላቱ አሰያየም በአዋጁ አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ /3/ እና /4/ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡ 2. The designation of the chairperson of the board and its other members listed under Sub Art. 1(a c) of this Article hereof shall be executed pursuant to Art. 9 Sub Arts. /3/ and /4/ of the Proclamation. www.abyssinialaw.com ገጽ-11- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -11 8. በቦርድ ስለሚከናወኑ ተግባራትና ስለሚሰጡ ውሳኔዎች 8. Duties to be Undertaken and Decisions to be Rendered by the Board ቦርዱ በአዋጁ የተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉትን ተጨማሪ ተግባራት ያከናውናል፡ Without prejudice to the duties and responsibilities vested to it by the Proclamation, the board shall carry out the following additional functions: 1. በአዋጁና በዚህ ደንብ ለቦርድ የተሰጡ ኃላፊነቶችን በአግባቡ መወጣት የሚያስችል ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያሳይ የአባላት የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ በማዘጋጀትና ተጠሪ በሆነው አካል በኩል በማጸደቅ ስራ ላይ ያውላል፣ 1. prepare a transparent and accountability oriented internal bylaw of members enabling to properly discharge those responsibilities entrusted to the board by the Proclamation and this Regulation; cause its approval by the body to whom it is accountable and thereby implement same; 2. በአዋጁ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ /6/ እና በቢሮው ተዘጋጅቶ በሚላከው መዋቅርም ሆነ ወደፊት በሚወጣ የስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የስራ አስኪያጅ ቅጥር፣ ምደባና ስንብትን በመፈጸም ለተጠሪው ያሳውቃል፣ 2. Undertake the recruitment, assignment and dismissal of managers in accordance with Art. 10 Sub Art. /6/ of the Proclamation and pursuant to the structure to be prepared and sent down by the Bureau as well as any subsequent managerial bylaw and thereby notify same to its superintendent; 3. በአዋጁ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ /11/ እና አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ /9/ መሰረት የሌሎችን የስራ መሪዎች ቅጥር፣ ምደባና ስንብት አስመልክቶ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ መሰረት በስራ አስኪያጅ የሚቀርበውን የውሳኔ አስተያየት መርምሮ ያጸድቃል፣ 3. Examine and approve the recommendation to be submitted by the manager pursuant to Sub Art. 2 of this Article regarding the recruitment, assignment and dismissal of other managers in accordance with Art. 10 Sub Art. 11 and Art. 13 Sub Art. 9 of the Proclamation; 4. በአዋጁ፣ በዚህ ደንብና ወደፊት በሚወጣው የስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እንዲፈጽምና እንዲያስፈጽም የተሰጡትን ኃላፊነቶች በአግባቡ በማይወጣ ማንኛውም የስራ መሪ ላይ በዚህና በስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንቦች ውስጥ ስለ አስተዳደራዊ 4. Cause the implementation of those provisions comprised in this Regulation and the managerial bylaw regarding the taking of administrative measures against any manager failing to properly discharge those responsibilities entrusted to him either to be implemented and have same implemented pursuant to the Proclamation, this www.abyssinialaw.com ገጽ-12- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -12 እርምጃዎች አወሳሰድ የተካተቱት ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ Regulation and such managerial bylaws as may subsequently be issued; 5. በየደረጃው የሚገኙትን የስራ መሪዎች የስራ አፈጻጸም ብቃት ለመለካት የሚያስችሉ መስፈርቶችን በማዘጋጀት የስራ አፈጻጸማቸውን በተገባው ውል መሰረት በየዓመቱ ይገመግማል፣ 5. Prepare criteria enabling to measure the efficiency of managers found at all levels and thereby evaluate their performance on an annual basis based on the contracts they may have concluded; 6. ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ /5/ በተገለጸው አግባብ የስራ መሪዎች አመታዊ የስራ አፈጻጸም ብቃት ዝቅተኛ ሁኖ በሚገኝበት ጊዜ በስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ላይ ስለዝቅተኛ የስራ አፈጻጻም ውጤት በሰፈሩት ድንጋጌዎች መሰረት በስራ መሪው ላይ ተገቢውን አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፣ 6. Possibly take an appropriate administrative measure in accordance with the provisions stipulated in the managerial bylaw concerning under performance against a manager where his performance is found to have been minimal pursuant to Sub Art. /5/ specified here above; 7. በአዋጁና በዚህ ደንብ ውስጥ ለቢሮው በተለይ ከተሰጠው መመሪያ የማውጣት ስልጣን ውጭ በሆኑ በሌሎች ጉዳዬች በጽ/ቤቱ ወይም በአማካሪዎች ተጠንቶ ሲቀርብለት የአሰራርና የአፈጻጸም መመሪያዎችን እያወጣ በስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣ 7. Issue working and implementation directives, where it receives a recommendation studied by the office or consultants thereof on those matters falling outside the directive-issuing powers specifically entrusted to the Bureau by the Proclamation and this Regulation as well as cause the implementation of same and follow up their implementation thereof; 8. የስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ይዘት ከአዋጁ፣ ከዚህ ደንብና ከሌሎች የሰራተኛ አስተዳደር መርሆዎች ጋር ተጣጥሞ መዘጋጀቱን ያረጋግጣል፣ 8. Ensure that the content of the managerial bylaw is prepared in compliance with the Proclamation, this Regulation and other principles of personnel administration; 9. ዝርዝሩ ይህን ደንብ ተከትሎ በቦርድ በሚወጣ የሰው ኃይል ስራ አመራርና አስተዳደር መመሪያ የሚገለጽ ሆኖ በአዋጁ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ /4/ መሰረት የጽ/ቤቱን ነባራዊና ወቅታዊ ሁኔታዎችና የተቋሙ አገልግሎት 9. With the details to be outlined in the human resource management and administration directive to be issued by the Board following this Regulation, possibly prepare, in accordance with Art. 7 Sub Art. 4 of the Proclamation, the size of man power, organization and structure necessary www.abyssinialaw.com ገጽ-13- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -13 አሰጣጥ የሚገኝበትን ደረጃ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚያስፈገውን የሰው ሀይል ብዛት፣ አደረጃጀትና መዋቅር ቢሮው ደረጃ ሰጥቶ ከሚልከው መዋቅር ጋር በተጣጣመ መንገድ በተጠሪው በኩል አስተያየት በማሰጠት ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡ for the office, in conformity with the structure ranked and sent down by the Bureau, taking into account the existing and current conditions of the office and the extent of the service delivery of the institution, to be commented by the body to which it is accountable; 10. ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ ከጠቅላላ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር የስራ ግምገማዎች እንዲካሄዱ ያደርጋል፡፡ 10. Cause the undertaking of performance evaluation with all employees of the office at least twice a year. 9. ስለ ቦርድ ተጠያቂነት 9. Accountability of the Board 1. የቦርድ አባላት በአዋጁና በዚህ ደንብ መሰረት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ካለመወጣቸው የተነሳ በአገልግሎቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት የግልና የጋራ ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል፡፡ 1. Members of the board shall have an individual and collective liability for the damage sustained to the service on account of their failure to discharge their responsibilities vested in accordance with the Proclamation and this Regulation. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሰረት የቦርድ አባላት በግልም ሆነ በጋራ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው በቦርዱ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ከሚወሰድባቸው አስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 2. Members of the board may, in accordance with Sub Art. 1 of this Article hereof, be liable under the law due to failure to discharge their individual or collective responsibilities apart from the administrative measures to be taken pursuant to the internal bylaw of the board. 10. በቦርድ ስለሚፈቀዱ ጥቅማጥቅሞች 10. Benefit to be permitted by the Board 1. ዝርዝሩ ይህን ደንብ ተከትሎ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ የሚገለጽ ሆኖ የስራ አመራር ቦርዱ፡ 1. With the details to be outlined by the directive to be subsequently issued by the Board following this Regulation, the board of management shall: ሀ/ የአዋጁን አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ /8/ እና አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ /18/ ድንጋጌዎች ተከትሎ በጽ/ቤቱ a. In compliance with the provisions of Art. 10 Sub Art. /8/ and Art. 12 Sub Art. /18/ of the Proclamation, examine and decide on www.abyssinialaw.com ገጽ-14- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -14 የሚቀርቡለትን የልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ክፍያዎች በተለይም፡ various benefit payments submitted to it by the office, in particular: አመታዊ የደመወዝ ጭማሪን i. Annual salary increments; የስራ መሪዎች የኃላፊነትና የሙያ አበል ii. Managerial and professional allowances; ሌሎች ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችና የማበረታቻ ክፍያዎች መርምሮ ይወስናል፤ iii. Other benefits and incentives; ለ/ በዓመቱ የተቀመጡትን ግቦች ለመለካት ይቻለው ዘንድ በየበጀት ዓመቱ ከስራ መሪዎች ጋር የስራ አፈጻጸም ውሎችን ይዋዋላል፡፡ b. Enter in to performance implementation contracts with the managers in each and every fiscal year so that it would be able to measure the goals set for the year. ሐ/ በአመታዊ የስራ አፈጻጸም ውሉ ውስጥ በተቀመጡት ግቦች አፈፃፀም አጥጋቢ እና ከአጥጋቢ በላይ ውጤት መኖሩ ሲረጋገጥ ለእያንዳንዱ የስራ መሪ መጠኑ በስራ አፈጻጸም ውልና በስራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ የሚወሰን የደመወዝ ጭማሪና የማበረታቻ ክፍያ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡ c. Cause the payment of the salary increment and other incentives whose amount has to be determined in the performance implementation contract and the managerial bylaw where it is confirmed that the achievement of those goals set in the annual work implementation contract is found to be satisfactory and above. 2. የሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪና የማበረታቻ ክፍያ ከጽ/ቤቱ ጋር በሚደረግ ድርድርና በሕብረት ስምምነታቸው መሰረት የሚወሰንና የሚፈጸም ይሆናል፡፡ 2. The payment of the salary increment and incentives of the employees shall be determined and executed pursuant to the negotiation to be conducted with the office and their collective agreements thereof. 11. ስለ ቦርድ አባላት አበል ክፍያ 11. Payment of allowance for Board Members 1. ለማንኛውም የቦርድ አባል በሚሰበሰብበት ጊዜ ብቻ የሚታሰብ የአባልነት አበል በወር አንድ ጊዜ ሊከፈለው ይችላል፡፡ 1. A membership allowance may be paid to every board member once in a month only for the time of his presence at a meeting. www.abyssinialaw.com ገጽ-15- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -15 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ የተገለጸው የአበል መጠን በዚህ ደንብ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ /1/ መሰረት በሚወጣው የቦርድ አባላት የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ቦርዱ ተጠሪ በሆነለት አካል ይወሰናል፡፡ 2. The amount of the allowance stated in Sub Art. /1/ of this Article hereof, shall be determined by the body to which the Board is accountable in accordance with the internal bylaw of board members to be issued pursuant to Art. 8 Sub Art. /1/ of this Regulation. 3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ ስር የተገለጸው ቢኖርም ያለበቂ ምክንያት በስብሰባ ላይ ሳይገኝ የሚቀር አባል ወርሃዊ የአበል ክፍያ አያገኝም፡፡ 3. Notwithstanding the provision of Sub Art. /2/ of this Article hereof, no payment of the monthly allowance be made to the member failing to be present at a meeting without sufficient cause. ክፍል ሦስት PART THREE ስለመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ደንበኞች፣ ስለአገልግሎት ክፍያና ስለኢንቨስትመንት ወጭ አመላለስ CUSTOMERS OF THE POTABLE WATER SUPPLY AND SEWERAGE SERVICES, SERVICE CHARGE AND RECOVERY OF THE INVESTMENT COST 12. የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ደንበኞች 12. Customers of the Potable Water Supply and Sewerage Services 1. በዚህ ደንብ መሰረት ከዚህ በታች የተመለከቱት የውሀ አገልግሎት ደንበኞች ናቸው፡ 1. The following are customers of the water supply service pursuant to this regulation: ሀ/ የመኖሪያ ቤት ደንበኛ፣ a. Residential customer ለ/ የመኖሪያ ቤት ያልሆነ ደንበኛ፣ b. Non-residential customer ሐ/ ከውኃ ማደያ ላይ ውኃ የሚጠቀም ደንበኛ c. Customer obtaining water supply from a public fountain. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የተመለከተው ቢኖርም ደንበኞች እንደየሚጠቀሙት የውኃ መጠን፣ እንደየተቋማቱ ባሕሪና የአመዳደብ ዓላማ 2. Notwithstanding the provision of Sub Art. 1 of this Article hereof, customers may further be broken down, depending on the volume of water they utilize, the character of their respective institutions and the objective of their www.abyssinialaw.com ገጽ-16- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -16 ወደፊት በሚወጡ መመሪያዎች ይበልጥ ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡፡ classification thereof pursuant to the directives to be issued subsequently. 13. የአገልግሎት ክፍያ 13. Service Charge 1. ማንኛውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በአዋጁና በዚህ ደንብ መሰረት ለሚሰጠው ማናቸውም አገልግሎት ከደንበኛው ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ የማስከፈል ስልጣን አለው፡፡ 1. Any Office of Potable Water Supply and Sewerage Service shall have the power to exact a reasonable amount of charge from its customers for every service it provides in accordance with the Proclamation and this Regulation. 2. ዝርዝር አፈጻጸሙ በመመሪያ የሚወሰን ሆኖ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የተጠቀሰው ቢኖርም በጽ/ቤቱ ተጠንቶ ሲቀርብለት ቦርዱ እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን ተመን በዓይነትና በመጠን በመለየት መርምሮ ያጸድቃል፡፡ 2. Notwithstanding the provision of Sub Art. /1/ of this Article hereof, the board shall, with the detailed implementation to be determined by a directive, examine and approve, as deemed necessary, the rate of various prices of service charges in type and amount, as and when it will have received same being studied and submitted to it on the part of the office. 3. በአዋጁ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ /9/ ስር የተገለጸው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ደንብና ደንቡን ለማስፈጸም በሚወጣ መመሪያ መሰረት በየደረጃው ስልጣን በተሰጠው አካል የጸደቀ የውኃ ታሪፍና የልዩ ልዩ አገልግሎቶች ተመን እንዳስፈላጊነቱ በየጊዜው ማስተካካያ ሊደረግበት ይችላል፡፡ 3. Without prejudice to the provision of Art. 10 Sub Art. /9/ of the Proclamation, the water tariff and the rate of the various services approved by the body authorized at each and every level on the basis of this Regulation and the directive to be issued for the implementation of same may be adjusted from time to time, as deemed necessary. 4. የውሃ ታሪፍ ዝርዝር አፈጻጸም ቢሮው በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ሆኖ ይህንን የሚመለከቱት መመሪያዎች ክልል አቀፍ ስርጭት ባለው ጋዜጣ ታትመው ለተገልጋዩ ሕዝብ ይፋ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ 4. With the detailed implementation of the water tariff decisions to be determined by a directive to be issued by the Bureau, the directives pertaining there to shall be published on a Gazette of a region wide circulation and officiated to the customers. www.abyssinialaw.com ገጽ-17- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -17 5. አግባብ ያለው የከተማ አገልግሎት ወይም መዘጋጃ ቤት ለኢንቨስትመንት፣ ለመኖሪያ ቤት እና ለሌሎች አገልግሎቶች ቀደም ሲል በምሪት ወይም በሊዝ በሰጣቸው አካባቢዎች የተዘረጉ የውሃ አውታሮችን ወይም መስመሮችን መለወጥ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ መልሶ ለመተካት የሚያስፈልገውን ወጪ በጽ/ቤቱ ሙያዊ ግምት መሰረት የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል፡፡ 5. The pertinent city service or municipality shall, where it has been found necessary to alter the previously installed water infrastructure or pipelines found in those plots of land it had rendered either by permit or lease for investment, dwelling and other purposes, have the duty to cover the cost necessary for the reconstruction of same based on the professional estimation of the office. 6. የሚመለከተው የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ መከላከያና ሌሎች አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ከተተከሉ ሃይድራንቶች የተጠቀሙበትን የውሃ ፍጆታ ወጭ የውሃ አገልግሎቱ በሚገጥመው ቆጣሪ በተመዘገበው መሰረት የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡ 6. The office of the city service or municipality concerned shall have the duty to pay the price of water utilized by them from hydrants planted to draw water with a view to rendering fire prevention and other services based on the reading registered in the water meter fitted by the water service. 7. ማንኛውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቀልጣፋ፣ ለደንበኞች ምቹነት ያለውና ጊዜ ቆጣቢ የሆነ የታሪፍና የአገልግሎት ክፍያ መሰብሰቢያ ስርዓት ይዘረጋል፡፡ 7. The Office of any Potable Water Supply and Sewerage Service shall put in place a tariff and service charge collecting system which is expeditious, suitable and time efficient in favor of the customers. 8. ማንኛውም ደንበኛ ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ /7/ በተገለጸው አግባብ የተጠቀመበትን የውኃ ፍጆታና የአገልግሎት ክፍያ ጽ/ቤቱ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ 8. Any customer shall, in accordance with Sub Art. /7/ here above, have the obligation to pay the price of water consumed and the service charge based on the time table set by the office. 9. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ /8/ መሰረት ወቅቱን ጠብቆ በማይከፍል ደንበኛ ላይ ውኃ አገልግሎቱ የውኃ አቅርቦቱን የማቋረጥና ያልተከፈለውን ተሰብሳቢ ሂሳብ በህግ አግባብ የማስመለስ ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ዝርዝሩ 9. The water service shall have the power to disconnect the supply of water and recover the unpaid arrears pursuant to law, as against the customer failing to make regular payments in accordance with Sub Art. /8/ of this Article www.abyssinialaw.com ገጽ-18- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -18 ይህን ደንብ ለማስፈፀም ቦርዱ በሚያወጣው የአፈፃፀም መመሪያ ይወሰናል፡፡ hereof. Particulars shall be determined in the implementation directive to be issued by the Board for the execution of this Regulation. 10. ደንበኛው የተጠቀመበት የውኃ መጠን በቆጣሪ ብልሽት ምክንያት በትክክል ሳይመዘገብ የተገኘ እንደሆነ ላለፉት ተከታታይ 6 ወራት በአማካይ በከፈለው መጠን ተሰልቶ ሂሳቡ ይከፈላል፡፡ ሆኖም ደንበኛው ውኃውን ከዚህ በፊት ከሚያውልበት ለተለየ ጠቀሜታ ማዋሉ ሲረጋገጥ የሚከፍለው የውኃ ፍጆታ ሂሳብ ቦርዱ ይህን ደንብ ተከትሎ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ 10. The customer shall, where the volume of water he had utilized is not found to have been accurately registered due to the fault of the water meter, pay the calculated average amount of which he has paid in the last 6 months; provided, however, that it is established that he had utilized the water for a purpose other than the usual one, the amount of money he has to pay shall be determined by a directive to be issued by the Board following this Regulation. 11. በማናቸውም ምክንያት የደንበኛውን የውኃ ፍጆታ የሚያመለክት የቆጣሪ ንባብ በሌለበት ጊዜ ሊከፍል የሚገባውን የፍጆታ ሂሳብ ጽ/ቤቱ የደንበኛውን አጠቃቀም አጣርቶ የተጠቀመበትን የውኃ ፍጆታ ክፍያ እንዲከፍል ይወስናል፡፡ 11. The office shall, in the absence of a meter reading capable of indicating the volume of water consumed by the customer, decide the payment for the water utilized by having examined the supposed consumption of the customer. 14. የሚሰበሰበውን ገቢ ለታቀደለት ዓላማ ስለማዋል 14. Deployment of Collected Revenue for the Intended Purpose 1. ማንኛውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት በአዋጁና በዚህ ደንብ መሰረት ከልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች የሚሰበሰበውን ገቢ ለቦርድ በማስፈቀድ በአዋጁ አንቀጽ 5 እና 12 መሰረት ለተዘረዘሩት ዓላማዎችና ተግባራት ማስፈጸሚያ የማዋል ግዴታ አለበት፡፡ 1. Any Potable Water Supply and Sewerage Service shall, upon causing the approval by the Board, have the duty to expend the income to be collected from various income sources pursuant to the Proclamation and this Regulation for the implementation of those objectives and duties specified under Arts. /5/ and /12/ of the Proclamation. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ የቦርዱ የቅድሚያ እውቅና ሳይኖረው ገቢውን ላልተፈለገ ዓላማ 2. A manager or an employee who has expended the income without the prior recognition of the Board for unintended purpose by breaching the www.abyssinialaw.com ገጽ-19- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -19 እንዲውል ያደረገ የስራ ኃላፊ ወይም ሰራተኛ በወንጀልም ሆነ በፍታብሄር ረገድ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ provision of Sub Art /1/ of this Article shall be liable under criminal and civil laws. 3. የማንኛውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት የስራ ኃላፊ በአዋጁ አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ /3/ መሰረት የተሰበሰበውን ገቢ አገልግሎቱ የተቋቋመለትን ተልእኮ ለማሳካትና ለዓላማዎቹ ማስፈጸሚያ ስለማዋሉ በየወቅቱ በኦዲት የማስመርመርና ውጤቱን ለቦርዱና ቦርዱ ተጠሪ ለሆነለት አካል የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ 3. The manager of any Potable Water and Sewerage Service shall have the responsibility to cause the timely auditing of the money collected pursuant to Art. 16 Sub Art. /3/ of the Proclamation, has expended for the attainment of the mission of which the service is established and for the implementation of objectives and thereby to notify the result to the Board and to the body to whom the board is accountable. 4. ማንኛውም የውኃ አገልግሎት ጽ/ቤት የሚጠቀምበትን የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ እና የውኃ ፍጆታ መክፈያ ሕትመት አቅም በፈቀደ መጠን ሕጋዊ፣ ዘመናዊ አሰራርን የተከተለና ተከታታይነት ያለው እንዲሆን ያደርጋል፡፡ 4. The office of any water service shall, as far as possible, cause the publication of its income collecting receipt and water consumption bill be legal, consistent with the modern working procedures and consecutively sequenced thereof. 5. የሂሳብ አሰራርና መዛግብት አያያዙን እንዲሁም ከነዚሁ ጋር ተያያዥነት ያለውን የንብረት አጠቃቀምና አስተዳደር የአዋጁን አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ /2/ ተከትሎ ቦርዱ በሚያወጣው የግዥና ንብረት አስተዳደር ማንዋል መሰረት ይፈጸማል፡፡ 5. The accounting and maintenance of books as well as the property utilization and administration related to same shall be executed in accordance with the Procurement and Property Administration Manual to be issued by the Board in conformity with Art. 16 Sub Art. /2/ of the Proclamation. 15. የረዥም ጊዜ ብድር አገልግሎት 15. Long Term Credit Service ማናቸውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት አቅም በፈቀደ መጠን የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ እንዲችል አገልግሎቱን በቀጥታ ለማግኘት የተወሰነ የገንዘብ ዕጥረት ያለባቸውን ደንበኞች በረዥም Any Office of the Potable Water Supply and Sewerage Service may, as far as possible, serve the customers with a limited shortage of money to acquire the service directly, by providing them a long term credit facility so as to be capable of making its service delivery expeditious and www.abyssinialaw.com ገጽ-20- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -20 ጊዜ የብድር አገልግሎት ሊያስተናግድ ይችላል፤ ዝርዝሩ ወደፊት በቦርዱ በሚወጣ የአፈፃፀም መመሪያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡ accessible. Particulars shall be outlined by a subsequent implementation directive to be issued by the Board. 16. የኢንቨስትመንት ወጪን ስለመተካት 16. Reimbursing Investment Cost 1. ማናቸውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ከዚህ ቀደም ለተገነቡም ሆነ ወደፊት ለሚገነቡ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የወጡ የኢንቨስትመንት ወጪዎችን በአዋጁ አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ /1/ እና አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀጽ /11/ የተደነገገውን ተከትሎ በቢሮው በየዓመቱ እንዲከፈል የተወሰነውን 50% የገንዘብ መጠን በበጀት ዓመቱ ላሉ ወራት በማከፋፈል በየወሩ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ ዝርዝሩ ይህንን ደንብ ተከትሎ ቢሮው ወደፊት በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡ 1. Any Office of the Potable Water Supply and Sewerage Service shall have the duty to reimburse, on monthly basis, the investment cost, 50% of which the bureau has decided to be paid annually in accordance with the provisions of Art. 16 Sub Art. /1/ and Art. 25 Sub Art. /11/ of the Proclamation, by having the total amount of money, expended for the construction of the potable water projects which were formerly constructed and those to be constructed afterwards, been divided over the months of the year. Particulars shall be determined by a subsequent directive to be issued by the Bureau following this Regulation. 2. የኢንቨስትመንት ወጪን ለመተካት በባንክ የሚቀመጠው ገንዘብ ወለድ የሚታሰብበት ይሆናል፡፡ 2. An interest shall be calculated on the money deposited in the bank for the purpose of reimbursing the investment cost. 3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በተቀመጠው የመክፈያ የጊዜ ገደብ ውስጥ ተቀማጭ ገንዘቡን ለመክፈል ያለበቂ ምክንያት ፈቃደኛ ሆኖ ባልተገß በማንኛውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የበላይ ኃላፊ ላይ ቢሮው በበላይነት ለሚመራው ቦርድና ቦርዱ ተጠሪ ለሆነለት አካል በማሳወቅ ተገቢ ነው ያለውን አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡ ያልተከፈለውን ተቀማጭ ገንዘብም ጽ/ቤቱ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ 3. The Bureau may take an administrative measure which it considers appropriate on any head of the Office of a Potable Water Supply and Sewerage Service who was found unwilling to pay the deposit in the prescribed time limit of payment pursuant to Sub Art. /1/ of this Article, with out sufficient cause, by having notified same to the governing Board and to the body to which the Board is accountable; provided, however, that the unpaid bill shall be collected from the office thereof. www.abyssinialaw.com ገጽ-21- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -21 4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ እና /2/ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ግንባታቸው ከዚህ በፊት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ጽ/ቤቶች የኢንቨስትመንት ወጪ የሚታሰበው ይህ ደንብ ከፀደቀ ጀምሮ ላለው ቀሪ የፕሮጀክት ዘመን ብቻ ይሆናል፡፡ 4. Without prejudice to Sub Arts. /1/ and /2/ of this Article hereof, the investment cost of those offices whose construction have been accomplished and started rendering service, shall be calculated only as regards the remaining duration of the project as of the date of this Regulation having been approved. 5. ቢሮው ከሚሰበስበው ገንዘብ ውስጥ በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርïት ችግር ላለባቸው የአገልግሎት ጽ/ቤቶች እንዳስፈላጊነቱ ፕሮጀክት ቀርፀው ሲያቀርቡና ይኸው አዋጪ መሆኑ ሲረጋገጥ ከጽ/ቤቶች ጋር በሚደረግ ስምምነትና ይህንኑ ለክልሉ መንግስት አቅርቦ በማፀደቅ በፕሮጀክት ዘመኑ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ገንዘብ በብድር ይሰጣል፤ ዝርዝሩ ይህን ደንብ ለማስፈፀም በቢሮው በሚወጣ መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡ 5. The Bureau shall, as deemed necessary, lend money out of the collected fund to be reimbursed in the project duration for those offices having the problem of potable water supply, against the agreement to be concluded with the offices, where the later will have prepared and submitted a project proposal and the feasibility of such project is confirmed, as well as the prior submittal and approval of same by the Regional Government. Particulars shall be determined by a subsequent directive to be issued by the Bureau for the implementation of this Regulation. 6. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ጽ/ቤቶች በራሳቸው ጥረት ከተለያዩ ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ወይም በሌላ ምክንያት ለፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ገንዘብ ተሰጥቷቸው ወይም ድርጅቱ ቢሰራላቸው ቢሮው በሚከፍተው የባንክ አካውንት የኢንቨስትመንት ወጫቸውን የማስቀመጥ ግዴታ ሲኖርባቸው የሚያስቀምጡትን ገንዘብ በፈለጉ ጊዜ በቢሮው አቅራቢነት ለክልሉ መንግስት በማስፈቀድ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፤ ዝርዝር አፈፃፀሙ ቢሮው በሚያወጣው መመሪያ ይገለፃል፡፡ 6. Without prejudice to Sub Art. /1/ of this Article hereof, the offices may utilize the money they have deposited in the bank account to be opened by the Bureau where they are obliged to deposit their investment cost acquired from various donor organizations using their own effort or having been donated for the project execution due to other reasons or where the organization by itself constructs the project, upon having the prior permission from the Regional Government through its submittal by the Bureau. Particulars shall be outlined by the directive to be issued by the Bureau. www.abyssinialaw.com ገጽ-22- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -22 17. ስለ ተቀማጭ ገንዘብ 17. Financial Deposit 1. ጽ/ቤቱ ከአዲስ መስመር ጠያቂ ደንበኞች የሚጠይቀው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ይህንን ደንብ ተከትሎ ቦርድ በሚያወጣው የማስፈፀሚያ መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡ 1. The amount of money of the financial deposit required by the office from the customers requesting for new-line connections shall be determined in the implementation directive to be issued by the Board following this Regulation. 2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ /1/ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለተቀማጭ ገንዘቡ ወለድ አይታሰብበትም፡፡ 2. Without prejudice to Sub Art. 1 of this Article hereof, interest may not be calculated on the deposit money. ክፍል አራት PART FOUR ስለመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎቶች አፈጻጸም THE IMPLEMENTATION OF POTABLE WATER SUPPLY AND SEWERAGE SERVICES 18. ስለ መጠጥ ውኃ አቅርቦትና የጥራት ደረጃ 18. Potable Water Supply and Quality Standard 1. ለከተማ ነዋሪ ህብረተሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲያቀርብ በአዋጁና በዚህ ደንብ ስልጣን የተሰጠው አካል የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ብቻ ነው፡፡ 1. The only organ authorized to provide potable water to urban dwellers, in accordance with the Proclamation and this Regulation, shall be the Urban Potable Water Supply and Sewerage Service. 2. በልዩ ሁኔታ በቢሮው የተፈቀደለት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሰው በክልሉ ከተሞች ውስጥ የውሃ መገኛ፣ ማጣሪያና ማከፋፈያ ተቋማትን መገንባትና ለራሱም ሆነ ለሌላ አካል የውሃ አገልግሎት ማቅረብ አይችልም፡፡ 2. No person may, unless specifically authorized to do so in consideration of his special interest by the Bureau, be able to construct a water source as well as purification and distribution centers or to provide water service to himself or to other bodies in any urban area of the Regional State. 3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ መሰረት የውሃ ተቋም ግንባታ እንዲያከናውን ቢሮው በልዩ ሁኔታ የሚፈቅደው ጉዳዩ የሚመለከተው ጽ/ቤት የውኃ አቅርቦቱን ለማዳረስ ከአቅሙ በላይ መሆኑን ሲያረጋግጥ ብቻ ነው፡፡ 3. The Bureau may, under exceptional circumstances, authorize the undertaking of a water supply facility construction pursuant to Sub Art. /2/ of this Article hereof, where it ascertains that the distribution of the water www.abyssinialaw.com ገጽ-23- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -23 supply is beyond the capacity of the office concerned. 4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 መሰረት በልዩ ሁኔታ የተፈቀደለት ሰው ቢሮው በሚያወጣው የውሃ ተመን መሠረት የውሃ አገልግሎት ክፍያ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ 4. A person who is specially authorized pursuant to Sub Arts. /2/ and /3/ of this Article shall be made to pay the water service charge in accordance with the water tariff to be issued by the Bureau. 5. ማንኛውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሠረት ለተጠቃሚው ህ/ሰብ የሚያቀርበው የመጠጥ ውሃ የፌዴራሉ መንግስት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያወጣውን የጥራት ደረጃ መመሪያ የጠበቀ ለመሆኑ በየወቅቱ ናሙና በመውሰድ ወይም በማስወሰድ በላብራቶሪ ምርመራ የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡ 5. Any Potable Water Supply and Sewerage Service shall have the responsibility to regularly verify, through the laboratory test of a sample taken, as to whether the potable water it supplies for the user community in accordance with Sub Art.1 of this Article that it meets the standards set in the guideline issued by the Federal Ministry of Water and Energy. 6. ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው የመጠጥ ውሃ ላይ ማናቸውም ብክለት እንዳይደርስ የውሃ አቅርቦት ተቋማትንና አካባቢያቸውን ለብክለት ከሚያጋልጥ ንክኪ ነፃ በሆነ መንገድ የመያዝና በሚያስተማምን ንጽህና የመጠበቅ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ 6. The office shall have the duty to handle the water-supplying centers and their surroundings in such a manner that they are free from the contact of any pollution-causing agents and thereby preserved with reliable sanitation. 7. ቢሮው በአዋጁ አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀጽ /9/ ድንጋጌ ስር በተሰጠው ስልጣን መሰረት ማናቸውም የውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት በሚያቀርበው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተፈላጊው የጥራት ጉድለት ያለበት መሆኑን ሲያረጋግጥ ተገቢ ነው የሚለውን ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡ ዝርዝሩ ይህንን ደንብ ለማስፈጸም ቢሮው በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡ 7. The Bureau shall, in accordance with the power vested in it under the provision of Art. 25 Sub Art. /9/ of the Proclamation, take a legal action it considers appropriate against any Water Service Office where it ascertains that the water which the later provides falls short of the required quality. Particulars shall be determined in the directive to be issued by the Bureau for the implementation of this Regulation. www.abyssinialaw.com ገጽ-24- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -24 19. ከገጠር ወረዳዎች ወደ ከተማ አስተዳደር የተከለሉ ቀበሌዎች የመጠጥ ውኃ አቅርቦት 19. Potable Water Supply for the Rural Woreda Kebeles Incorporated in to Urban Administrations 1. ማናቸውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በአዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ /17/ ድንጋጌ መሰረት ከገጠር ወረዳ ወደ ከተማ አስተዳደር ለተከለሉ አካባቢዎች የተሟላ ንጹህ የመጠጥ ውኃ የማቅረብና የውኃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡ 1. Any Office of the Potable Water Supply and Sewerage Service shall, in accordance with the provision of Art. 12 Sub Art. /17/ of the Proclamation, have the responsibility to supply sufficient potable water for those rural woreda areas incorporated in to the boundary of urban administration and get them become beneficiaries thereof. 2. ማናቸውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ከዚህ ቀደም የተገነቡትንም ሆነ ወደፊት የሚገነቡትን ወደ ከተማ አስተዳደር የተጠቃለሉ የገጠር ቀበሌዎች የውኃ ተቋማት በኃላፊነት ተረክቦ ለዚሁ ዓላማ አግባብነት ያላቸውን ባለሙያዎች በመመደብ የማስተዳደር፣ የመንከባከብና የመጠገን ግዴታ አለበት፡፡ 2. Any Office of the Potable Water Supply and Sewerage Service shall, upon taking over same with responsibility and assigning employees appropriate for the purpose, have the obligation to administer, preserve and maintain the water supply facilities of those rural kebeles incorporated in to the boundary of urban administration which are earlier constructed and to be constructed afterwards. 3. በአዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ /17/ መሰረት ከገጠር ወረዳ ወደ ከተማ አስተዳደር የተከለሉ የገጠር ቀበሌዎችን የውኃ ተቋማት ለመገንባት የሚያስፈልጉት የኢንቨስትመንት፣ የኦፕሬሽንና አስተዳደራዊ ወጭዎች ከዚህ በታች በተገለፁት አካላት እንዲሸፈኑ ይደረጋል፡ 3. The investment, operation and administrative costs required to construct the water supply facilities of the rural woreda kebeles incorporated in to the boundary of urban administration shall be covered by the following organs specified here below: ሀ/ ለግንባታ የሚያስፈልጉት የኢንቨስትመትና የልዩ ልዩ ስልጠና ወጭዎች ………….. …አግባብ ባለው የከተማ አስተዳደር፣ a. The investment cost and such costs as are required for the construction and various training expenses, …………… by the urban administration pertaining thereto; www.abyssinialaw.com ገጽ-25- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -25 ለ/ የባለሙያዎች ደመወዝ እና የሌሎች ጥቅማጥቅሞች ወጪዎች……….. አግባብ ባለው የውኃ አገልግሎት፣ b. Expenses of salary and other benefits of the professionals ……………..by the water service pertaining thereto; ሐ/ የኦፕሬሽን እና የጥገና ወጭዎች……….. በሚመለከታቸው የውኃ ተጠቃሚዎች፡፡ c. Operational and maintenance costs………. by the water users concerned. 20. ለደንበኞች የውኃ ቆጣሪ ስለሚቀርብበት፣ ስለሚተከልበት ቦታና ስለሚጠበቅበት ሁኔታ 20. Provision of Water–Meter for Customers, Place of its Installation and Protection 1. ማናቸውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በዚህ ደንብ መሠረት የሚያቀርበውን የውሃ መጠን ለመቆጣጠር የሚያስችለው የውሃ ቆጣሪ መሳሪያ በደንበኞቹ የውሃ መስመር ላይ ይገጥማል፡፡ 1. Any Office of the Potable Water Supply and Sewerage Service shall, in accordance with this Regulation, install water-meter on water pipelines of its customers so as to control the volume of water it provides there with. 2. አግባብ ካለው የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የቅድሚያ እውቅናና ፈቃድ ውጪ በአንድ የውሃ መስመር ላይ የተገጠመን የውሃ ቆጣሪ መቀየር ወይም እንዲቀየር ማድረግ በዚህ ደንብ የተከለከለ አድራጐት ነው፡፡ ዝርዝሩ ይህንን ደንብ መሠረት በማድረግ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይገለጻል፡፡ 2. Changing or causing the change of the water meter installed on water pipelines without prior cognizance and approval of the pertinent office of potable water supply and sewerage service is an act prohibited by this Regulation. Particulars shall be provided for in a directive to be issued by the Board on the basis of this Regulation. 3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ የሰፈሩትን ድንጋጌዎች በመተላላፍ ውኃን በሕገወጥ መንገድ ጥቅም ላይ ማዋሉ ወይም ማባከኑ የተደረሰበት ማንኛውም ሰው ወይም ደንበኛ ውሃውን ለማምረት፣ ለማጣራትና ለማሰራጨት ጽ/ቤቱ ያወጣውን ሙሉ ወጪ በሙያዊ ግምት መሰረት የመክፈል ግዴታ አለበት ፡፡ 3. Any person or customer whose act of illegally using or wasting the water has been established in contravention of the provisions specified in Sub Art. 2 of this Article hereof, shall have the obligation to pay the full cost which the office may have spent to produce, purify and distribute the water on the basis of the professional estimate. 4. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /2/ እና /3/ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም ደንበኛ፡ 4. Without prejudice to the provisions of Sub Arts. /2/ and /3/ of this Article hereof, the office may take a legal action extending to the www.abyssinialaw.com ገጽ-26- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -26 termination of the contract against any customer where: ሀ/ በአገልግሎት ጽ/ቤቱ የተገጠመለትን ቆጣሪ አዙሮ ከገጠመ ወይም እንዲገጠም ካደረገ፤ a. Installs by reversing or causes the reversed installation of the water-meter fitted for his use by the office of the service; ለ/ ቆጣሪውን ወደ ኋላ አዙሮ በመግጠም እንዲተረተር ካደረገ ወይም ካስደረገ፤ b. Unwinds or causes the unwinding of the water meter by fixing it anticlockwise; ሐ/ ከቆጣሪው በፊት ባዕድ የውኃ ማስተላለፊያ መስመር ከቀጠለ ወይም እንዲቀጠል ካደረገ፤ c. Connects or causes the connection of strange water transmitting pipeline before the water meter; መ/ እሽጉን ካላቀቀ ወይም እንዲለቅ ካደረገ፤ d. Detaches the pack or causes the detachment of same; ሠ/ በሌላ ማናቸውም መንገድ ማናቸውንም አይነት ጉዳት በቆጣሪው ላይ ካደረሰ ወይም እንዲደርስ ካደረገ የአገልግሎት ጽ/ቤቱ ደንበኝነቱን እስከ ማቋረጥ የሚደርስ ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድበት ይችላል፡፡ e. Damages the water meter or causes any type of damage on same in whatever means. 5. የውሃ ቆጣሪ እንዲያቀርብ በደንበኛ ጥያቄ የቀረበለት ጽ/ቤት ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ እና የእቃውን ዋጋ በማስከፈል በተቻለ ፍጥነት ምላሽ ይሰጣል ፡፡ 5. The office which has been served with a request by customers to provide water-meter shall respond by charging the proper service fee and the price of the materials, as soon as possible. 6. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 ስር የተደነገገው ቢኖርም ጽ/ቤቱ የተጠየቀውን የውኃ ቆጣሪ በወቅቱ ለማቅረብ ያልቻለ እንደሆነ ጥራቱ በጽ/ቤቱ አማካኝነት የተረጋገጠለትን የውኃ ቆጣሪ ደንበኛው በራሱ ወጪ በግሉ ገዝቶ የማስገጠም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 6. Notwithstanding the provision of Sub-Art. 5 of this Article hereof, where the aforementioned Office is unable to provide with the requested water meter on time, the customer shall be entitled to buy the water-meter and have it installed with its quality having been approved by the office at his own expense. 7. የውሃ ቆጣሪ የሚተከልበትን ቦታ ጽ/ቤቱ ይወስናል፡፡ 7. The office shall determine the place where the water meter is to be installed. www.abyssinialaw.com ገጽ-27- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -27 8. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 7 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በደንበኛው ላይ ችግር እንዳያስከትል ቆጣሪው ከዋና በር እስከ 3 ሜትር ገባ ብሎ ባለው እርቀት አመቺ ቦታ ላይ ሊተከል ይችላል፡፡ 8. Without prejudice to the provision of Sub Art. 7 of this Article hereof, the water meter may be installed on the suitable place entering up to 3 meters from the main gate not to cause difficulties on the customer. 9. ለደንበኛው የሚዘረጋው የቧንቧ ስፋት ቢሮው ወይም የውኃ አገልግሎቱ በሚያወጣው ቴክኒካዊ ማንዋል መሰረት ይወሰናል፡፡ 9. The width of the pipe to be installed for the customer shall be determined on the basis of the technical manual to be issued by the Bureau or the water service. 10. ጽ/ቤቱ ከቆጣሪ በፊትም ሆነ በኋላ የተዘረጉ የውሃ መስመሮችን የመፈተሽ፣ የመመርመርና የመቆጣጠር ስልጣን ይኖረዋል፡፡ 10. The office shall have the power to inspect, to calibrate and to control over the water pipelines installed before and after the water meter. 11. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /10/ የተገለጸው ቢኖርም ማንኛውም ደንበኛ ከቆጣሪ በኋላ የውኃ መስመር በሚዘረጋበት ወቅት ለውኃ ብክነት ወይም ብክለት ያልተጋለጠ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲቻል ይህንኑ በቅድሚያ ለአገልግሎቱ የማሳወቅና የማማከር ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም በማናቸውም ጊዜ በሚደረግ ፍተሻ ብክነት ወይም ብክለት መኖሩን የአገልግሎት ጽ/ቤቱ ሲያረጋግጥ ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡ 11. Notwithstanding the provision of Sub-Art. /10/ of this Article hereof, any customer shall, in advance, have the responsibility to notify and consult the service while installing a water pipeline after the water meter so as to make sure that the pipeline is not exposed for wastage or pollution; provided, however, that the office of the service may take an appropriate rectification measure when ascertaining the existence of wastage or pollution by proving same through inspection to be conducted any time. 21. የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ መስመር የመዘርጋትና የመጠገን መብት 21. Right to Install and Maintain Potable Water Supply and Sewerage Pipelines 1. ከቆጣሪ በኋላ በመኖሪያ ቤትና በግቢ ያለውን የውሃ መስመር የመዘርጋትና የመጠገን ሃላፊነት የደንበኛው ይሆናል፡፡ 1. The installation and maintenance of water pipeline located in the dwelling and premises after the water meter shall be the responsibility of the customer. www.abyssinialaw.com ገጽ-28- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -28 2. ከቆጣሪ በፊት ያለው የውሃ መስመር የደንበኛው ይዞታ ሆኖ ሲገኝ የጥገናውን ሙሉ ወጪ ደንበኛው ይሸፍናል፡፡ ዝርዝሩ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ፡፡ 2. The customer shall cover the full maintenance cost where the water pipeline located before the water meter is found to be in his possession. Particulars shall be determined by the directive to be issued by the Board. 22. የመጠጥ ውሃና የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን ስለመዘርጋት 22. Installing Potable Water Supply and Sewage Transmitting Pipelines 1. በከተማ ክልል ውስጥ የሚዘረጉ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የከተማውን መሪ ፕላን ተከትለው መዘርጋት ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም እነዚህን መስመሮች ለመዘርጋት ዕቅድ ያለው ማናቸውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጉዳዩ የሚመለከተውን የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት በቅድሚያ ማማከር ይኖርበታል፡፡ 1. The installation of potable water supply and sewage transmitting pipelines in an urban center shall be installed in compliance with the requirements indicated in the master plan of the city. To this end, any potable water supply and sewerage service wishing to install these pipelines shall, in advance, consult the office of the city service or the municipality concerned. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የተደነገገው ቢኖርም መሪ ፕላን ከመዘጋጀቱ አስቀድሞ የተሰሩ መኖሪያ ቤቶች የከተማው ማዘጋጃ ቤት መሪ ፕላን እስኪያዘጋጅ ድረስ ውሃ የማግኘት መብታቸውን ለማስጠበቅ ሲባል ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ጋር በመመካከር የውኃ አገልግሎቱ የውሃ መስመር የመዘርጋት ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡ 2. Notwithstanding the provision of Sub-Art. /1/ of this Article hereof, the water service shall, in consultation with the concerned body, have the responsibility to install water pipeline for the houses constructed prior to the preparation of a master plan in order to secure the right of having water until the municipality shall have prepared the master plan. 3. የትራፊክ እንቅስቃሴ ጐልቶ በሚታይበት በማናቸውም አካባቢ የሚዘረጉ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ ማስተላለፊያ ቧንቧዎች በተገቢው ጥልቀት በመሬት ውስጥ መቀበር ይኖርባቸዋል፡፡ ዝርዝሩ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ፡፡ 3. The potable water and sewerage transmitting pipelines to be installed at any place of which is largely exposed for heavy traffic activity shall be buried in the appropriate depth beneath the ground. Particulars shall be determined by a directive to be issued by the Board. www.abyssinialaw.com ገጽ-29- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -29 4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /3/ የተመለከተው ድንጋጌ ቢኖርም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ባጋጠመ ጊዜ የውሃ ብክነት ወይም ብክለት እንዳይፈጠር ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የመጠጥ ውሃና የፍሳሽ ማስተላለፊያ ቧንቧ ሳይቀበር በመሬት ላይ ሊዘረጋ ይችላል ፡፡ 4. Notwithstanding the provision of Sub-Art. /3/ of this Article hereof, potable water and sewerage transmitting pipelines may be laid unburied on the surface of the ground where cases attributable to force majeure, by making the appropriate precaution against the occurrence of undesirable wastage or pollution of water. 23. በሌላ ሰው የይዞታ መሬት ላይ የውኃ መስመር የመዘርጋት መብት 23. Right to Install Water Pipeline on the Land Holdings of Another Person 1. ማናቸውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የከተማውን መሪ ፕላን ተከትሎ በማናቸውም የይዞታ መሬት ላይ የውኃና ፍሳሽ መስመሮችን የመዘርጋትና የማስተላለፍ ስልጣን ይኖረዋል፡፡ 1. Any Potable Water Supply and Sewerage Service shall have the power to install and transmit water and sewer pipelines in a land holding of any person based on the master plan of the city. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የተገለጸው ቢኖርም መስመሮችን በሚዘረጋበትና በሚያስተላልፍበት ወቅት በንብረት ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት ተገቢውን ካሳ የመክፈል ወይም ንብረቱን እንደነበረ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡ 2. Notwithstanding the provision of Sub-Art. /1/ of this Article hereof, the service shall have the responsibility to pay the appropriate compensation for the damage caused to the property while installing and transmitting pipelines or otherwise to rearrange the property as it had been before. 3. ማንኛውም የመሬት ይዞታ ባለቤት በይዞታው ስር የተዘረጉ የውኃ መስመሮች እንዳይበላሹ አስፈላጊውን ትብብር የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡ በሆነ ምክንያት ሲበላሹም የመስመሩ ባለቤት ለሆነው የውኃ አገልግሎትና ለሚመከተው አካል ሳይዘገይ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ 3. Any owner of the land holding shall, as of necessity, have the duty to cooperate in such a way that the water pipelines installed in his holding may not be dysfunctional thereof; provided, however, that where they go wrong due to any cause, he shall be duty-bound to notify to the water service which happens to be in charge of the line and to the pertinent body without delay. www.abyssinialaw.com ገጽ-30- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -30 4. ማንኛውም የግል የይዞታ መሬት ባለቤት በቂ ምክንያት ከሌለው በስተቀር የትኛውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት መስመሮችን ለመዘርጋት፣ ለመጠቀም፣ ለመቆጣጠርና ለመንከባከብ ወይም ለመጠገን የሚያደርገውን ስራ ማደናቀፍ አይችልም፡፡ 4. Any owner of private land holding shall, unless he has sufficient cause, not obstruct the installation, utilization, supervision and preservation activities of lines to be undertaken by any Office of the Potable Water Supply and Sewerage Service. 5. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /4/ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ጽ/ቤቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዳይሰጥ በሚያደናቅፍ ማንኛውም ሰው ላይ ይህንን ደንብ ተከትሎ በሚወጣ መመሪያ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡ 5. An administrative measure may, in accordance with a directive to be issued following this Regulation, be taken against any person who obstructs the smooth service delivery of the office by breaching the provision of Sub Art. 4 of this Article hereof, 24. የውሃ መስመሮችን ስለማጋራት 24. Sharing Water Pipelines 1. ደንበኛው ወጪውን ችሎ በተዘረጋለት በማናቸውም የውሃ መስመር ላይ ሌላ ደንበኛ ለመጠቀም ሲያመለክት አግባብ ያለው የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጥያቄ የቀረበበት መስመር ከአንድ በላይ ለሆኑ ደንበኞች በቂ ውሃ የማጋራት አቅም ያለው መሆኑን ያረጋገጠ እንደሆነ አዲሱ ደንበኛ ለመስመሩ ባለቤት ደንበኛ ከመስመሩ ግምት የድርሻውን በመክፈል የውሃ መስመር ማስዘርጋት ይችላል፡፡ ዝርዝሩ ይህን ደንብ ተከትሎ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ 1. Where a new customer applies for utilization of a pipeline already installed at the expense of another original customer and where the pertinent Potable Water Supply and Sewerage Service, whom the latter has approached for same, verifies that the line desired for use has got the capacity to supply adequate water for more than one customers, the new customer may be made to share the line after having in advance paid the total cost and thereby refunded the former customer to the extent of his own portion. Particulars shall be determined by a directive to be issued by the Board following this Regulation. 2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ /1/ ስር የተደነገገው ቢኖርም የውኃ መስመር የተዘረጋበት ቦታ ለሌላ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ወይም የከተማ አስተዳደሩ የመስመሩን አጠቃላይ ወጪ እንዲሸፍን ይደረጋል፡፡ 2. Notwithstanding the provision of Sub Art. /1/ of this Article hereof, where the plot on which the water pipeline has been installed is delivered for other purposes, the beneficiary of the service or the urban administration shall cover the full cost of the line installation. www.abyssinialaw.com ገጽ-31- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -31 25. ስለመጠጥ ውሃና ፍሳሽ መስመሮች ደህንነት 25. Safety of Potable Water Supply and Sewage Pipelines በዚህ ደንብ መሠረት የተዘረጉትን የመጠጥ ውሃና የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች ወይም ሌሎች ተዛማች ስራዎች ሆነ ብሎ ወይም በግዴለሽነት የሰበረ፣ የቆረጠ፣ ያበላሸ ወይም ሌላ ማናቸውንም አይነት ጉዳት ያደረሰባቸው ማንኛውም ሰው ወደፊት ይህንን ደንብ ለማስፈጸም በቦርዱ በሚወጣ መመሪያ ከሚወሰድበት አስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ Whosoever intentionally or by negligence breaks, disrupts, spoils or causes any other obstruction with regard to potable water and sewage transmitting pipelines installed or other related works shall, apart from the administrative measure to be taken against him on the basis of a subsequent directive to be issued by the Board for the implementation of this Regulation, be liable in accordance with the relevant laws. 26. የውኃ መስመር ስለማዛወር፤ ማሻሻልና መለወጥ 26. Relocation, Improvement and Alteration of Water Pipelines 1. በቂ በሆነ ምክንያት እና በሌላ ሕግ እንዳይከፈል ካልተደረገ በስተቀር የውኃ መስመር ለማዛወር፣ ለማሻሻል፣ ለማስፋፋት ወይም ለመለወጥ የሚያስፈልገው ወጪ የውኃ መስመር እንዲዛወርለት፣ እንዲሻሻልለት፣ እንዲስፋፋለት ወይም እንዲለወጥለት በጠየቀው ወገን ይሸፈናል፡፡ ዝርዝሩ ይህንን ደንብ ተከትሎ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ 1. The costs required to relocate, improve, extend or alter a water pipeline shall, unless such payment has been set aside due to sufficient cause and other law, be covered by the party requesting for the relocation, improvement, extension or alteration of the water pipeline. Particulars shall be determined by the directive to be issued by the Board following this Regulation. 2. የዚህን አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ ተከትሎ ሲፈፀም የሌላ ሶስተኛ ወገን የግል መስመር የሚነካ ከሆነ በጽ/ቤቱም ሆነ በሶስተኛው ወገን አነሳሽነት የሚደረገውን የመስመር ማዛወር በመስመሩ ማዛወር የሚነካው ደንበኛ በቅድሚያ እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡ 2. Should the relocation of the pipeline implemented pursuant to Sub Art. /1/ of this Article affect the line belonging to other third party, such relocation to be undertaken with the initiation of the office or the third party shall, in advance, be notified to the customer affected by same. www.abyssinialaw.com ገጽ-32- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -32 3. በጽ/ቤቱ የተዘረጋ የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ መስመር አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ወይም ውኃው እንዲበከል ያደረገ ሰው የሚወሰድበት ሕጋዊ እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ምክንያት መስመሩን ማዛወር አስፈላጊ ሲሆን ጥፋት ፈጻሚው ወጭውን እንዲሸፍን በማድረግ እንዲዛወር ይደረጋል፡፡ 3. Without prejudice to the legal action to be taken on a person who causes the termination and pollution of water on the pipeline installed by the Office of the Potable Water Supply and Sewerage Service, and if it is thus necessary to relocate the line due to such cause, the relocation shall be made upon making the offender cover the expense thereof. 27. የውሃ መገኛ ቦታዎችን ስለመከለል 27. Enclosing Water Sources 1. ማናቸውም የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የውኃ መገኛ ቦታዎችን ከበካይ ነገሮች ንኪኪ ለመከላከል ይቻል ዘንድ እንደየሁኔታው በተወሰነ ርቀት በሁሉም አቅጣጫዎች እያንዳንዱን የውኃ መገኛ ቦታና ተቋም ሊከልል ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት፡ 1. The Office of any Potable Water Supply and Sewerage Service may, in consultation with the appropriate bodies, enclose every water source area and facility within the limit of a certain radius, under the circumstances, so as to protect the water from contact of the possible contaminating agents thereof. To this effect, the protective delineation shall be: ሀ/ ለውሃ ማደያ ጣቢያዎች ………ከማደያው መሃል ጀምሮ በ10 ሜትር ራዲየስ፣ a. With regard to public fountains ---------10 meters radius from the center of the fountain; ለ/ ለማጠራቀሚያ ጋኖች ……………ከጋኖቹ መሃል ጀምሮ ከ 30 እስከ 50 ሜትር ራዲየስ፣ b. With regard to reservoirs 30 through 50 meters radius from the center of the reservoir; ሐ/ ለሞተር ቤቶች …………… ከቤቶቹ መሃል ጀምሮ ከ30 እስከ 50 ሜትር ራዲየስ፣ c. With regard to pumping houses 30 through 50 meters radius from the center of the house; መ/ ለውሃ መገኛ ምንጮች ……….ከምንጮቹ መሃል ጀምሮ ቢያንስ 350 ሜትር ራዲየስ፣ d. With regard to water sources at least 350 meters radius from the center of the source; ሠ/ ለውሀ ጉድጓዶች …………. ከጉድጓዶቹ ቢያንስ 100 ሜትር ራዲየስ ተከልለው እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡ e. With regard to water wells at least 100 meters radius from the well; www.abyssinialaw.com ገጽ-33- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -33 2. ቀደም ሲል በዙሪያው የተለያዩ ግንባታዎችና የኢንቨስትመንት ስራዎች በመከናወናቸው ምክንያት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ከፊደል ተራ ቁጥር /ሀ/ እስከ /ሠ/ በተመለከተው መሰረት ለመፈጸም ያልተቻለ እንደሆነ ግንባታውን የሰሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የውሃ መገኛ ቦታዎችን ከሚበክል ከማናቸውም ንኪኪ ነፃ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል፡፡ 2. Where it is impossible to execute in accordance with Sub Art. 1 (a-e) of this Article as a result of previously undertaken constructions of different kind and investment projects, the enterprises or individuals who may have constructed same shall have the responsibility to ensure that the activities carried out by them are free from any contact of polluting agents. 3. በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር አካላት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ እና /2/ መሠረት የውሃ መገኛ ቦታዎችና ተቋማት ተከልለው እንዲጠበቁ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ፡፡ 3. The administrative bodies found at various levels shall, in accordance with Sub Arts. /1/ and /2/ of this Article hereof, have the responsibility to cause the enclosure and preservation of water sources and facilities. 28. የውኃ ብክነትን ስለመከላከል 28. Preventing Wastage of Water 1. ማንኛውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የውሃ ብክነትን ለመቆጣጠር የሚያስችል የአፈፃፀም እቅድ በየአመቱ እያዘጋጀና ግብ እያስቀመጠ ለዚሁ ስኬታማነት የመስራት ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡ 1. Any Potable Water Supply and Sewerage Service shall have the responsibility to prepare action plans and set goals on a yearly basis with a view to controlling the wastage of water and working for the success thereof. 2. ማንኛውም የውሃ አገልግሎት ደንበኛ በተዘረጋለት መስመር ላይ በቧንቧ ብልሽትም ሆነ በሌላ በማናቸውም ምክንያት ውሃ ሲፈስ ያጋጠመው እንደሆነ ወዲያውኑ አግባብ ላለው የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡ ይህን ባያደርግ ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት የህዝብ ሀብት እንዲባክን በማድረጉ ለባከነው ውሃ በሙያ ግምት መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 2. Any customer of a water service shall, upon finding out leakage of water along the pipeline in his favor due to either damage or some other cause, have the responsibility to report same to the appropriate office of potable water supply and sewerage service forthwith; provided, however, that failing to do so, he shall be liable for the wastage of the water as per the professional estimate due to his intentional or negligent act. www.abyssinialaw.com ገጽ-34- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -34 29. የመጠጥ ውሃ ብክለትን ስለመከላከል 29. Averting Contamination of Potable Water 1. የመጠጥ ውሃ በፍሳሽ ቆሻሻ እንዳይበከል የውሃ መስመሮች ከፍሳሽ ማስተላለፊያ ቧንቧዎችና ቦዮች በጐንም ሆነ በከፍታ በቂ እርቀት ኖሯቸው ይዘረጋሉ፡፡ 1. Pipelines of potable water supply shall have a desirable distance from any sewage transmitting pipes and channels, horizontally or vertically, with a view to preventing same from possible contamination. 2. በከተማ ዉስጥም ሆነ በአካባቢው የውኃ አቅርቦትን ሊበክሉ የሚችሉ የግል እና የድርጅት የውኃ ጉድጓዶችና ፍሳሾች ሲኖሩ ጽ/ቤቱ ከሚመለከተው የከተማ አስተዳደርና አግባብ ካለው ዞን የውኃ ሃብት ልማት መምሪያ ወይም በደረጃው ከሚገኝ የውኃ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ጋር በመመካከር ሊያሳግድ ወይም ሊያስወግድ ይችላል፡፡ 2. Where there are individual and organizational water wells and sewers in an urban center and its surroundings that may possibly contaminate the supply of potable water therein, the office may, in consultation with the concerned urban administration and the pertinent zonal water resource development department or the water resource development office found at the given level, cause their suspension or elimination. 30. የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ስለሚቀርብበት ሁኔታ 30. Condition of Providing Sewerage Disposal Service 1. ማናቸውም የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በተናጠል ወይም አግባብ ካላቸው ሌሎች የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር በዚህ ደንብ መሠረት የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል፡፡ 1. Any Urban Potable Water Supply and Sewerage Service may, in accordance with this regulation, provide a sewage disposal service separately or in collaboration with other concerned government organs. 2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የግል አገልግሎት ሰጪዎች በፍሳሽ ማስወገድ ስራ ከመሰማራት ሊያግዳቸው አይችልም፡፡ 2. The provision of sub-Art. 1 of this Article may not impede against those private service providers having a legal license from engaging on sewage disposal activity. 3. ጽ/ቤቱ በየትኛውም ከተማ የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት የሚያቀርበው የወቅቱን የገበያ ዋጋ መሰረት በማድረግ የሚያወጣውን ተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ በማስከፈል ይሆናል፡፡ 3. The office shall provide sewage disposal service in any urban center by exacting a reasonable service charge determined and issued on the basis of the current market price. www.abyssinialaw.com ገጽ-35- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -35 31. የፍሳሽ አወጋገድ ስለሚፈፀምበት ሁኔታ 31. Implementation of Sewage Disposal 1. በየትኛውም ከተማ ውስጥ በፍሳሽ መቀበያና ማስተላለፊያ ቧንቧዎች፣ ቦዮች ወይም የማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች የሚሰበሰብ፣ የሚተላለፍ ወይም የሚጓጓዝ ማናቸውም ፍሳሽ የአካባቢውን የተፈጥሮ ሃብት በማይበክልበት እንዲሁም የህብረተሰቡን ጤንነትና የአካባቢን ጽዳት በማይጐዳበት ሁኔታ መወገድ ይኖርበታል፡፡ 1. Any urban sewage captured, transmitted or transported by capturing and transmitting pipes, sewers or transporting vehicles shall be disposed in such a way that it may not contaminate the natural resources of the environment as well as adversely affect the health of the community and sanitation of the surroundings. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ድንጋጌ መሠረት የሚካሄደው ፍሳሽ የማስወገድ እንቅስቃሴ በተፈጥሮ አካባቢም ሆነ በህዝብ ጤንነት ላይ ለሚያደርሰው ማናቸውም ጉዳት አገልግሎቱ ወይም ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው የግል አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ባለቤት አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 2. The Service or owner of the licensed private service-providing enterprise shall be liable pursuant to pertinent laws for any damage it has caused on the natural environment and on the public health while carrying out sewage disposal activity pursuant to the provision of sub-Art. 1 of this article hereof. 32. ስለተከለከሉ ተግባራት 32. Prohibited Activities 1. ደንበኛው የሚከተሉትን ተግባራት እንዳይፈጽም በዚህ ደንብ ተከልክሏል፡ 1. The customer is prohibited, by this regulation, not to perform the following activities: ሀ/ ያለ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎቱ የቅድሚያ ዕውቅናና ፈቃድ የተዘረጋለትን የውሃ መስመር ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት ወይም ከዚሁ መስመር ላይ ሌላ ሰው እንዲቀጥልበትና በውሃው እንዲጠቀም ማድረግ ወይም የውኃውን መስመር ከተዘረጋበት ስፍራ ማዛወር፣ a. Transferring one's water pipeline to another person or allowing the other person to extend from the same pipeline and to utilize the water or relocating the water pipeline without prior cognizance and approval of the Water and Sewerage Service; ለ/ የሚቀርብለትን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ከጓሮ አትክልቶች ማጠጫነትና ማስዋቢያነት አልፎ ለመደበኛ መስኖ ልማት እንዲውል ማድረግ፣ b. Employing the safe, drinking water provided hereof for the purpose of normal irrigation development, apart from using it to water horticultural seedlings and beautifying gardens. www.abyssinialaw.com ገጽ-36- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -36 ሐ/ ከቆጣሪ በፊት ካለ የውኃ መስመር ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወይም በስርቆት ውኃን መጠቀም፡፡ c. Utilizing water from the water pipeline located before the water-meter in an improper way or theft. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ የተከለከሉትን ተግባራት የፈጸመ ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 2. Any person who carries out the prohibited activities in contravention of the provision of Sub Art. /1/ of this Article hereof shall be liable under the pertinent laws. 33. በመጠጥ ውኃና ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ወቅት ስለሚደርስ ጉዳት ካሳ 33. Compensation for Damage Sustained whilst Installing Potable Water and Sewage pipelines 1. ማንኛውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችን ለመዘርጋት ከሚመለከተው አካል አስፈቅዶ በሚሰራበት ጊዜ በቁፋሮ ስራ ምክንያት በመንገዶች ላይ ለሚያደርሰው ማናቸውም ጉዳት ተገቢውን ካሳ ይከፍላል ወይም የተበላሸውን መንገድ በነበረበት ሁኔታ መልሶ የመገንባት ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡ 1. Any Potable Water Supply and Sewerage Service shall have to pay compensation equivalent to the harm sustained on the roads whilst digging the ground, upon having the permission from the pertinent body, in order to install potable water and sewage transmission pipelines or have the responsibility to reconstruct the road in a condition it had been before. 2. በደንበኛው ጥያቄ የውኃ መስመር ለመዘርጋት መንገድ የሚቆፈር ሲሆን ደንበኛው እንደ መንገዱ ዓይነት መንገዱ የሚቆፈርበትንና ተመልሶ የሚገነባበትን አግባብ ባለው አካል የተወሰነውን ግምት ለጽ/ቤቱ ከፍሎ አስፈላጊውን አገልግሎት ሊያገኝ ይችላል፡፡ 2. Where the water pipeline has to be installed up on the request of the customer and a road has thus to be dug, the customer may acquire the necessary service upon paying to the office the cost, for the digging and maintenance of the road estimated by the appropriate body, depending on the type of the road. www.abyssinialaw.com ገጽ-37- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -37 34. ስራዎችን በሌላ አካል ስለማስፈፀም 34. Outsourcing of Activities ማንኛውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው እንደውሃ ተቋማት ጥገና፣ የውሃ ቦኖ ማደያዎች፣ የውሃ ሽያጭ፣ የቆጣሪ ንባብ፣ የውሃ ሂሳብ አሰባሰብ፣ ልዩ ልዩ ጥናቶች፣ ዲዛይኖች፣ ግንባታዎች፣ የፅዳትና የጥበቃ ስራዎችን ህጋዊ ፈቃድ ላላቸው ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በህግ መሠረት መስጠትና ማሠራት ይችላል፡፡ Any Potable Water Supply and Sewerage Service may, where it finds it essential, outsource by law such activities as the maintenance of water facilities, public fountains, water sale, water-meter reading, collection of water charges, a variety of studies, designs, constructions, safety and guarding to be undertaken by other organizations that are licensed to render similar services. 35. ቢሮው ስለሚሰጣቸው የቴክኒክ ድጋፎች 35. Technical Support to be Rendered by the Bureau ቢሮው በአዋጁ አንቀጽ 25 እና በሌሎች ሕጎች የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ለመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን የቴክኒክ ድጋፎች እንዳስፈላጊነቱ ሊሰጥ ይችላል፡ The bureau may, without prejudice to the duties and responsibilities vested in it under Art. 25 of the Proclamation and other laws, provide, as deemed necessary, such technical support to the potable water and sewerage services as are specified here below: 1. በከተማም ሆነ በገጠር የሚታየውን የስራ አመራርና የሂሳብ አሰራር የአቅም ክፍተት ለመሙላት በራሳቸው በአገልግሎቶቹ ጥያቄ ወይም በራሱ አነሳሽነት የአቅም ግንባታ ስራዎችን ያካሂዳል፣ 1. Carryout capacity building activities with a view to filling the capacity gaps in respect of the managerial and financial affairs prevailing both in the urban and rural settings, be it upon the request of the Services themselves or through its own initiation; 2. የዉሃ አገልግሎቶቹ የውኃ መሳቢያ ጄኔሬተርና የፓምፕ ግዥ ለመፈፀም በማይችሉበት ጊዜ ውክልና ሲሰጠው ግዥ ሊፈጽም ይችላል፣ 2. Possibly carryout the procurement of water pulling generator and pumps through delegation, at such times when the water services are unable to execute those duties; 3. እንደሁኔታው ጥያቄ ሲቀርብለት በየደረጃው ከሚገኙ የውኃ ሃብት ልማት ጽ/ቤቶችና የውኃ አገልግሎቶች አቅም በላይ የሆኑ የጥገናና የሪሃብሊቴሽን ስራዎችን በሚመለከታቸው ጽ/ቤቶች ወጪ ያከናውናል፣ 3. Undertake, upon request, having due regard to the circumstances, those maintenance and rehabilitation works beyond the capacity of the water resource development offices and water services at various levels, with the expenses to be covered by the office concerned; www.abyssinialaw.com ገጽ-38- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -38 4. ከውኃ አገልግሎት ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን የከተሞች የዉኃ ታሪፍ እንዲጠናና በአዋጁ መሰረት ታሪፍ እንዲያጸድቅ ስልጣን ለተሰጠው አካል እንዲቀርብ በማድረግ እንዲጸድቅና በስራ ላይ እንዲውል ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡ 4. Follow up and provide support, in collaboration with the water services, for the approval and implementation of the urban water tariff, upon first causing same to be studied and thereby submitted to the body authorized by the Proclamation to approve the rate thereof. 36. ስለአገልግሎት አሰጣጥ 36. Service Delivery ማናቸውም የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በዚህ ደንብ መሠረት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለደንበኞቹ ግልጽነት የተሞላበትና በቅልጥፍና የሚያከናዉን መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአገልግሎት አሰጣጥ እስታንዳርድ በማዘጋጀት በቦርዱ አስጸድቆ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ Any Office of Potable Water Supply and Sewerage Service shall prepare a service rendering standard enabling to insure the complete transparency and expeditiousness of the service to be delivered pursuant to this Regulation for its customers as well as implement same upon its approval by the Board. ክፍል አምስት PART FIVE ስለገጠር መጠጥ ውሃ ጣቢያ ኮሚቴዎች ምስረታና ስለስራ መሪዎች አደረጃጀት ESTABLISHMENT AND ORGANIZATION OF THE RURAL POTABLE WATER STATION COMMITTEES AND THEIR MANAGERS 37. ስለገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ ጣቢያዎች አመራር 37. Management of The Rural Potable Water and Sewerage Stations 1. የገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ ጣቢያዎች የሚመሩት በአዋጁና በዚህ ደንብ መሠረት የእያንዳንዱ ጣቢያ ተጠቃሚ ሕብረተሰብ በሚያቋቁማቸው የውሃ ኮሚቴዎች አማካኝነት ይሆናል፡፡ 1. Rural Potable Water and Sewerage Stations shall be managed by the water committees to be established on the part of the water user community benefiting from each and every station as per the Proclamation and this Regulation. www.abyssinialaw.com ገጽ-39- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -39 2. የአዋጁ አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ /1/ እና /2/ በሚደነግገው መሠረት እያንዳንዱ የውሃ ኮሚቴ ከ 5 - 7 የሚደርሱ አባላት የሚኖሩት ሲሆን ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር አብዛኛዎቹ ሴቶች መሆን አለባቸው፡፡ 2. Each water committee shall, pursuant to what is provided under Art.19 sub-Arts. /1/ and /2/ of the Proclamation, have members numbering from 5 through 7; provided, however, that the majority of whom must, if that is not beyond possibility, be women. 3. ኮሚቴው የራሱን ሰብሳቢ፣ ፀኃፊ፣ ሂሳብ ሹም፣ ንብረት ክፍልና ገንዘብ ያዥ ከአባላቱ መካከል በምርጫ ይሰይማል፡፡ 3. The committee shall designate its own chairperson, secretary, accountant, store keeper and cashier from among the membership through election. 4. ኮሚቴው በጋራ ስብሰባ በሚያሳልፋቸው ውሳኔዎችና በስራ ክፍፍሉ መሰረት እያንዳንዱ አባል የእለት ተዕለት ተግባሩን ያከናውናል፡፡ 4. Each and every member shall carry out his day to day duties based on the collective decisions passed by the committee and the division of work thereof. 38. የኮሚቴው ስብሰባ 38. Meetings of the Committee 1. ኮሚቴው በአዋጁ አንቀጽ 21 ንዑስ አንቀጽ /2/ ላይ በተደነገገው መሰረት ቢያንስ በየወሩ 1 ጊዜ ይሰበሰባል፤ 1. The committee shall convene its meeting at least once a month in accordance with Art. 21 Sub Art. /2/ of the Proclamation. 2. አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የኮሚቴው ሰብሳቢ ስብሰባዎችን ሊጠራ ይችላል፤ 2. The chairperson of the committee may call for extra ordinary meetings, as deemed necessary. 3. የኮሚቴው ምልዓተ ጉባኤ የሚሆነው ቢያንስ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት የኮሚቴው አባላት ሲገኙ ብቻ ነው፤ 3. There shall be a quorum only where two-third of the committee members are present. 4. ማናቸውም ውሳኔ የሚያልፈው በስብሰባው ላይ ከተገኙት የኮሚቴው አባላት ከግማሽ በላይ ድምጽ ሲደገፍ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ድምጹ እኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል፡፡ 4. Every decision shall be passed where it is supported by more than half the vote of the committee members present at the meeting. In case of a tie, however, the chair person shall have a casting vote. www.abyssinialaw.com ገጽ-40- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -40 39. ስለኮሚቴ አባላት የአገልግሎት ዘመን 39. Tenure of the Committee Members የኮሚቴው አባላት የአገልግሎት ዘመን 3 ዓመት ይሆናል፡፡ ሆኖም ማናቸውም አባል ከታመነበት ለዳግመኛ የአገልግሎት ዘመን ሊመረጥ ይችላል፡፡ The tenure of the committee members shall last three years; provided, however, that any member may, on having been confided upon, be re-elected for the second term. ክፍል ስድስት PART SIX ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች MISCELANEOUS PROVISIONS 40. ስለ አስተዳደራዊ እርምጃዎችና ቅጣቶች 40. Administrative Measures and Penalties 1. የአዋጁንና የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች የጣሰ ማንኛውም ሰው እንደ ጥፋቱ ደረጃ እየታየ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት መከሰሱ ሳይቀር ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ እስከገንዘብ መቀጮና አገልግሎቱን እስከማቋረጥ ሊደርስ የሚችል አስተዳደራዊ እርምጃ ሊወሰድበት ይችላል፡፡ 1. Any person in violation of the provisions of the Proclamation and this regulation may, apart from having been charged in a competent court pursuant to the relevant laws depending on the degree of his offence, be subjected to an administrative measure reaching up to a monetary fine and the termination of the service starting with reprimand, as deemed necessary. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሰረት በገንዘብ መቀጮ የሚወሰደው አስተዳደራዊ እርምጃ በውኃ መስመሮች ላይ ለደረሰው ጉዳትና ለባከነው ውኃ በሙያ ግምት የሚከፈለውን የካሳ ገንዘብ አያስቀርም ፡፡ 2. The administrative measure to be taken pursuant to Sub Art. /1/ of this Article hereof may not impede the compensation to be paid for the damage of water pipelines and for the wastage of water on the basis of a professional estimate. 3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ እና /2/ መሰረት ጥፋት ተፈጽሞ ሲገኝ የተለየ ስርዓት መከተል ሳያስፈልግ በደንብ ተላላፊዎች ላይ ለውኃ አገልግሎቱ ገቢ የሚሆን የገንዘብ መቀጮ እንዲጣል 3. It is hereby decided to impose a monetary fine to form part of the revenue of the water service against petty offenders without following a specific procedure, where an offence is found to have been committed in accordance with Sub Arts. /1/ and /2/ of this Article hereof. The www.abyssinialaw.com ገጽ-41- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -41 ተወስኗል፡፡ የመቀጮው መጠንም ሆነ የሚወሰደው አስተዳደራዊ እርምጃ የእያንዳንዱን የጥፋት ዓይነትና ክብደት መሰረት በማድረግ ወደፊት ቢሮው ይህንን ደንብ ለማስፈጸም በሚያወጣው ዝርዝር መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡ amount of fine and the administrative measure shall, on the basis of the type and severity of each offence, be determined in a subsequent specific directive to be issued by the Bureau for the implementation of this Regulation. 41. ስለ ውሳኔዎች ተፈጻሚነት 41. Execution of Decisions የጽ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎች፣ ቦርዱና ቢሮው በዚህ ደንብ መሰረት በየደረጃው የሚሰጧቸው ውሳኔዎች፣ ትዕዛዞችና የማስተካካያ እርምጃዎች ወዲያውኑ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ The decisions, instructions and remedial measures rendered by the office heads, the board and the bureau at all levels pursuant to this Regulation shall be implemented promptly. 42. የውሳኔዎች አለመፈጸም ስለሚያስከትለው ውጤት 42. Effect of Non-Compliance of Decisions 1. በዚህ ደንብ መሰረት ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጦ ውሳኔ የተሰጠበት ማንኛውም ሰው የተወሰነበትን የገንዘብ መቀጮ ወዲያውኑ በሕጋዊ ደረሰኝ መክፈል ይኖርበታል፡፡ 1. Any person found guilty of violating this regulation and penalized as such shall promptly pay the monetary fine against lawful receipt. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ የተመለከተውን ግዴታ ያልፈጸመ ማንኛውም ሰው በዚህ ደንብ መሰረት የተወሰነበትን የገንዘብ መቀጮ መክፈሉ ሳይቀር ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ቀርቦ አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 2. Any person who has not discharged the obligation as stated under Sub Art. /1/ of this Article shall, apart from having paid the fine imposed on him pursuant to this regulation, stand before a competent court and liable to pertinent law. 43. የመተባበር ግዴታና የወንጀል ሃላፊነት 43. Duty to Cooperate and Criminal Responsibility 1. ማንኛውም ሰው ይህንን ደንብና ደንቡን ለማስፈጸም የሚወጡ መመሪያዎችን ስራ ላይ በማዋል ረገድ የመተባባር ግዴታ አለበት፡፡ 1. Any person shall have the duty to cooperate in the implementation of this regulation and the directives to be issued for the implementation of the Regulation. www.abyssinialaw.com ገጽ-42- ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ቁጥር 9 ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No, 9 18th Day of May 2014, Page -42 2. የዚህን ደንብና ደንቡን ለማስፈጸም የሚወጡ መመሪያዎችን ድንጋጌዎች የጣሰ ወይም አፈጻጸማቸውን ያሰናከለ ማንኛውም ሰው በዚህ ደንብና አግባብ ባለው የወንጀል ህግ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 2. Any person acting in violation of the provisions of this regulation and directives to be issued for the implementation of this Regulation or obstruct their implementation shall be liable on the basis of this regulation and appropriate criminal law. 44. ስለተሻሩና ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጐች 44. Repealed and Inapplicable Laws 1. የከተማና ገጠር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ማደራጃ አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ቁጥር 34/1997 ዓ.ም ተሽሮ በዚህ ደንብ ተተክቷል፡፡ 1. The Urban and Rural Potable Water Supply and Sewerage Services’ Organizing Proclamation Implementation Regulation No. 34/2005 is hereby repealed and replaced by this Regulation. 2. ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሌላ ደንብ፣ መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሰራር በዚህ ደንብ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ 2. No other regulation, directive or customary practice in contravention of this regulation shall be applicable with respect to matters covered therein. 45. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ 45. Effective Date ይህ ደንብ በክልሉ መንግስት ዝክረ-ህግ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡ This Regulation shall come into force as of the date of its publication on the Zikre-Hig Gazette of the Regional State. ባህርዳር DDoonnee aatt BBaahhiirr DDaarr ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም. TThhiiss 1188tthh ddaayy ooff MMaayy,, 22001122 አያሌው ጎበዜ AAyyaalleeww GGoobbeezziiee የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት HHeeaadd ooff GGoovveerrnnmmeenntt ርዕሰ መስተዳድር ooff tthhee AAmmhhaarraa NNaattiioonnaall RReeggiioonnaall SSttaattee www.abyssinialaw.com