تخطَّ إلى المحتوى
Nelum
قوانين إثيوبيا

Forestry Enterprise Establishment, Council of Regional Government Regulation No 70/2009

صدر في 2009-10-13 · النص بتاريخ 2026-10-01

القانون العام والإرشادات الرسمية منشورة بوصفها أبحاثاً. ليست مشورة قانونية أو ضريبية أو مالية.

البحث نفسه مكتوب بالإنجليزية. العناوين والوسوم مترجمة؛ أما النتائج والاقتباسات فغير مترجمة.

عن هذا القانون

اللغة
English
النوع
لائحة
الدولة
إثيوبيا · Amhara
الموضوعات
Agricultural and rural development, Forestry
الكلمات المفتاحية
agricultural development, forest management/forest conservation, institution, timber, timber extraction/logging, afforestation/reforestation, agro-forestry, business/industry/corporations, sustainable development, governance
الفئات
*

أين تقرؤه

    لا يوجد رابط مصدر مسجل لهذا القانون.

النص

نص القانون نفسه، مادةً مادة، كما هو محفوظ. لكل مادة رابطها.

  1. ገፅ-1- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -1 በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዝክረ-ሕግ ZIKRE-HIG OF THE COUNCIL OF THE AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE IN THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA የአንዱ ዋጋ ብር 13.28 Price Birr በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ISSUED UNDER THE AUSPICES OF THE COUNCIL OF THE AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE የፖ.ሣ.ቁ. 312 P.O.Box ማውጫ ደንብ ቁጥር 70/2002 ዓ.ም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደን ኢንተርፕራይዝ ማቋቋሚያ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት ደንብ CONTENTS Regulation No. 70/2009 The Amhara National Regional State Forestry Enterprise Establishment, Council of Regional Government Regulation. ደንብ ቁጥር 70/2002 ዓ.ም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደን ኢንተርፕራይዝን ለማቋቋም የወጣ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ Regulation No. 70/2009 A COUNCIL OF REGIONAL GOVERNMENT REGULATION ISSUED TO PROVIDE FOR THE ESTABLISHMENT OF THE FORESTERY ENTERPRISE IN THE AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE. 15ኛ ዓመት ቁጥር 1 15 th year No. 1 ባህር ዳር ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Bahir Dar 13 th , Oct.2009 www.abyssinialaw.com ገፅ-2- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -2 ክልሉ በደን ልማት ረገድ ያለውን ጂኦ-ኢኮሎጂያዊ አቅም ተጠቅሞ የደኑ ሴክተር ለህዝቡ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት መፋጠን የሚፈለግበትን አስተዋጽኦ ማከርከት የሚችልበትን እድል ማመቻቸት በማስፈለጉ፤ Whereas, it has been necessary that the region, having utilized its geo-ecological potential with regard to forestry development, has to facilitate an opportunity for the forestry sector to enable it to make a contribution, required of it, for the acceleration of the economic and social development of the people therein; በክልሉ ውስጥ ለሚቀረፁት የደን ልማት ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያ የደን ሴክተሩ ራሱ በቂ ሃብት የሚያመነጭበትን ተቋም መፍጠር በማስፈለጉ፤ Whereas, it has become necessary to create an institution whereby the forestry sector itself generate adequate resource for the execution of forestry development programs to be formulated in the Region; በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ሥፍራዎች ለምተው የሚገኙትን የመንግስት ደኖች ለአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል በማስፈለጉ፤ Whereas, it has become necessary to properly put to use those public forests which are developed and found at various place in the Region so that they shall make a contribution to the locality with respect to the latter’s social and economic development thereof; በክልሉም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእንጨትና በእንጨት ውጤቶች አቅርቦትና ፍላጐት መካከል እያደገ የመጣውን ክፍተት ለመሙላት ጠንካራ የደን ልማት ተቋም መፍጠር በማስፈለጉ፤ Whereas, with a view to filling the ever increasing gap between supply and demand in wood and wood products at the regional and national levels, it is necessary to create a strong forestry development institution thereof; በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እየተበራከተ የመጣውን ሥራ አጥነት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ሰፊ የሥራ እድል መፍጠር የሚያስችል ልማት ማካሄድ በማስፈለጉ፤ Whereas, it has become necessary to carry out development efforts that would enable to create a multitude of job opportunities with the view to reducing the ever growing unemployment in all areas of the Region; በክልሉ ውስጥ ክፉኛ ተራቁቶ የሚታየውን የመሬት ክፍል በደን በመሸፈን የአካባቢ ተሃድሶን ማምጣትና መሬቱን ለተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲውል ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤ Whereas, it has been appropriate to bring about an environmental revival and cause the land to be used for better economic benefits by covering that part of the land which is adversely destitute in the region with the afforestation thereof; www.abyssinialaw.com ገፅ-3- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -3 በሥራ ላይ ያለው ኋላቀር የደን ልማትና አጠቃቀም ሥርዓት ሳይንሳዊና ቀልጣፋ በሆነ አስተዳደር የሚደግፍ ሞዴል በመፍጠር አሠራሩን ማሻሻልና ዘመናዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤ Whereas, it has been necessary to revise and modernize the working system by creating a model which may support the existing backward forestry development system in a scientific and efficient administration; በክልሉም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲታይ የግሉ ዘርፍ በደን ልማትና ኢንቨስትመንት በኩል የሚያሳየው ተሣትፎ አናሳ ከመሆኑ የተነሳ የመንግስትን ቀጥተኛ ተሣትፎ የሚጠይቅ ስለሆነ ራሱን የቻለና ንብረትነቱ የክልሉ መንግስት የሆነ የደን ኢንተርፕራይዝ ማቋቋምና በተወዳዳሪነት እንዲሠራ ማድረግ በማስፈለጉ፤ Whereas, due to the fact that the private sector participation in the forestry development and investment is insignificant, when evaluated at the regional and national levels, and it thus requests direct participation of the government, it has been necessary to establish forestry enterprise which is autonomous and owned by the Regional State; የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተሻሻለው የብሔራዊ ክልሉ ህገ-መንግስት አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ (7) ድንጋጌ ሥር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል። Now, therefore, the Council of the Amhara Regional Government, in accordance with the powers vested in it under the provision of art.58, sub. Art. 7 of the Revised Constitution of the National Regional State, hereby issues this regulation. ክፍል አንድ ጠቅላላ PART ONE GENERAL 1. አጭር ርዕስ 1. Short Title ይህ ደንብ “የደን ኢንተርፕራይዝ ማቋቋሚያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 70/2002 ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። This regulation may be cited as “The Forestry Enterprise Establishment, Council of Regional Government Regulation No 70/2009.” 2. ትርጓሜ፣ 2. Definition የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚሁ ደንብ ውስጥ፦ Unless the context otherwise requires, in this regulation: www.abyssinialaw.com ገፅ-4- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -4 1. “ቦርድ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የሚቋቋመው የኢንተርፕራይዙ ሥራ አመራር ቦርድ ነው። 1. “Board” shall mean the managing board of the enterprise to be established in accordance with art. 8, sub-art.1 of this regulation hereof. 2. “ቢሮ” ማለት የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ነው። 2. “Bureau” shall mean the Regional Bureau of Agriculture and Rural Development. 3. “ደን” ማለት በተፈጥሮ የበቀሉ ወይም ተተክለው የለሙ በአብዛኛው የዛፎችና ሌሎች የእንጨትነት ጠባይ ያላቸው ተክሎች የሚገኙበት የእጽዋት ክምችት ነው። 3. “Forest” shall mean a collection of plants in which the majority of trees and other plants of wooden characteristic are found, having either naturally grown or being planted and developed, as the case may be. 4. “ዛፍ” ማለት በዓይነቱ በዕድሜውና በመጠኑ ሳይለይ የእንጨት ጠባይ ያለው ሲሆን ቀርቀሃ፣ ዘንባባና ኤጀንስው ዛፍ ብሎ የሚሰይመውን ማናቸውንም ተክል ሊጨምር ይችላል። 4. “Tree” shall mean any such thing that has a characteristic of wood without categorization as to its type, age and size and may include bamboo, palm tree and any plant that the Agency may designate as such. 5. “የደን መሬት” ማለት ለደን ልማትና ጥበቃ ተብሎ የተከለለና በደን የተሸፈነ አካባቢ የቁጥቋጦ መሬትንና በከፍተኛ ተዳፋት ላይ የሚገኙና የተራቆቱ መሬቶችን ይጨምራል። 5. “Forestland” shall mean an area which is reserved for development and protection of forest and thereby covered therewith and may include shrub lands; those areas situated at highly- sloppy and degraded lands. 6. “የመንግስት ደን” ማለት በክልሉ መንግስት ባለቤትነት ሥር የዋለ ማናቸውም ጥብቅ ወይም ምርት ሰጪ ደን ነው። 6. “Government Forest” shall mean any reserve or productive forest which is under the ownership of the Regional State. 7. “የደን ውጤት” ማለት ዛፍ ወይም የዛፍ ተፈጥሯዊ አካል የሆነ ወይም እንጨት ያልሆነ ማንኛውም ምርት ወይም በመጀመሪያ ደረጃ በሰው እጅ የተመረተ ወይም በፋብሪካ የተዘጋጀ የደን ምርት ነው። 7. “Forest Product” shall mean any product of a tree or natural part thereof or a non wood one or a forest product manually made on a primarily level or processed by a factory. www.abyssinialaw.com ገፅ-5- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -5 ክፍል ሁለት PART TWO ስለ ብሔራዊ ክልሉ የደን ኢንተርፕራይዝ መቋቋም፣ ዓላማ፣ ተግባርና ድርጅታዊ አቋም Establishment, Objective, Duties And Organizational Structure Of The National Forestry Enterprise 3. ስለመቋቋም 3. Establishment 1. የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደን ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በኋላ “ኢንተርፕራይዙ” እየተባለ የሚጠራ ራሱን የቻለና ህጋዊ ሰውነት ያለው የክልሉ መንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል። 1. The Amhara National Regional State Forestry Enterprise, / hereinafter referred to as “The Enterprise”/is hereby established as an autonomous government enterprise having its own personality under this regulation. 2. ኢንተርፕራይዙ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ሆኖ ተጠሪነቱ በዚህ ደንብ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የክልሉ መንግስት ለሚሰይመው ቦርድ ይሆናል። 2. The Enterprise shall be established for indefinite period of time and be accountable to the board to be designated by the Regional State in accordance with art. 8 sub- Art. 1 of this regulation. 4. መነሻ ካፒታል 4. Initial Capital 1. ኢንተርፕራይዙ በክልሉ መንግስት የተመደበለትን ጥሬ ገንዘብ ብር 76,339,163 (ሰባ ስድስት ሚሊዬን ሦስት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሽህ አንድ መቶ ስልሳ ሦስት ብር) እና በዓይነት የመንግስት ደኖችን መነሻ መስሪያ ካፒታሉ አድርጐ ተቋቁሟል። 1. The Enterprise is hereby established with its initial working capital being Birr 76,339,163 (seventy six million, three hundred thirty nine thousands and one hundred sixty three Birr) allocated for it by the regional government in cash along with the government forests in kind. www.abyssinialaw.com ገፅ-6- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -6 5. ዓላማዎች 5. Objectives ኢንተርፕራይዙ በዚህ ደንብ መሠረት የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፦ The Enterprise shall, pursuant to this regulation, have the following objectives: 1. ደንና የደን ውጤቶችን በስፋት በማልማት፣ በማምረትና እሴት በመጨመር የክልሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ማፋጠን፣ 1. To accelerate the economic and social development of the region by extensively developing and producing forest and forest products as well as by increasing value to same. 2. ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ሥራ አጥነትን መቀነስና የክልሉን ህብረተሰብ ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ 2. To reduce the level of unemployment and thereby ensure sustainable gains of the Regional Community by creating wider job opportunities. 3. በክልሉም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእንጨትና በእንጨት ውጤቶች አቅርቦትና ፍላጐት መካከል እያደገ የመጣውን ክፍተት ማጥበብ፣ 3. To narrow the ever growing gap between supply and demand in wood and wood product at regional as well as national levels; 4. ደንና የደን ውጤቶችን እሴት ጨምሮ በማምረት ወደ ውጭ በመላክና ከውጭ የሚገባውን በመተካት የውጭ ምንዛሬ አቅምን ማዳበር። 4. To enhance foreign exchange capacity by producing forest and forest products, with an increasing value, exporting same and substituting the imported ones. 6. የኢንተርፕይራዙ ተግባርና ኃላፊነት 6. Duties and Responsibilities of the Enterprise ኢንተርፕራይዙ በዚህ ደንብ አንቀጽ (5) ሥር እንደተደነገገው የተቋቋመባቸውን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ይቻለው ዘንድ ከዚህ በታች የተመለከቱት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፦ The Enterprise shall have the following duties and responsibilities with a view to discharging the objectives specified under art.5 of this regulation hereof; 1. ለማገዶ፣ ለኮንስትራክሽንና ለፋብሪካ ፍጆታ በጥሬ ዕቃ ምንጭነት የሚያገለግሉና 1. Establish and develop planting sites for various tree species and those ones usable www.abyssinialaw.com ገፅ-7- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -7 የተለያዩ የዛፍ ዝርያዎች ተከላ ቦታዎችን ያቋቁማል፣ ያለማል፣ for firewood, construction and for manufacturing consumption raw material sources; 2. በክልሉ መንግስት ይዞታ ስር ከሚገኙት ደኖች ውስጥ ለምርት የሚሆኑትን ተረክቦ ተገቢውን የማኔጅመንት ፕላን በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ 2. Take charge of those forests capable of being used for production out of the forests under the ownership of the government and cause same to be utilized and exploited by preparing the appropriate management plan thereof; 3. ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ደኖች ማልማት የሚያስችል የደን መሬቶችን በመለየት የሚመለከተውን አካለ አስፈቅዶ የማልማት ሥራ ያከናውናል፤ 3. Having identified those forestlands enabling to develop forests and bring about economic benefits and thereby secured permission from the bodies concerned, carry out development activities thereof; 4. የዱር ሙጫ፣ እጣን፣ ባዮፊውልና ኢሰንሻል ኦይል በማምረትና በማዘጋጀት ረገድ የንግድ ሥራዎች ያካሂዳል፤ 4. Cary out business activities by producing and preparing wild-gum, incense, bio-fuel and essential oil; 5. እንጨትንና እንጨት ያልሆኑ የደን ውጤቶችን ወደ ተለያዩ የምርት ዓይነቶችና ደረጃዎች የሚቀይሩ ፋብሪካዎችንና ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም ምርቱን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል፤ 5. Supply the product to domestic and foreign markets by having planted factories and industries capable of processing and altering wood and non-wood forestry products into various kinds and categories of products. 6. የዛፍ ዘር፣ የማስጌጫና ሌሎች የዛፍና ቁጥቋጦ ችግኞችን ያለማል፣ በነዚሁም ይነግዳል፤ 6. Develop the tree species and other decorating tree and shrub seedlings and thereby conduct business with them; 7. በእጣንና በሙጫ ዛፎች የተሸፈኑ ደኖችንና የደን መሬቶችን ተረክቦ ዘላቂነት ባለው መንገድ ያለማል፣ ያስተዳድራል፤ 7. Take over those forests covered with incense and gum trees and forestlands, develop and manage same in a sustainable manner; 8. ከፋብሪካዎችና ከኢንዱስትሪዎች ፍላጐት አንፃር የጥሬ ዕቃ ምንጭነትን መሠረት 8. Encourage forestry development efforts to be carried out by farmers, institutions and small scale developers with the view to www.abyssinialaw.com ገፅ-8- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -8 ለማስፋት የሚያስችልና በአርሶ አደሩ፣ በተቋማትና በአነስተኛ አልሚዎች በኩል የሚካሄድ የደን ልማትን ያበረታታል፤ enabling to the expansion of raw material source-base from the standpoint of the demands by factories and industries; 9. ከደን ልማትና ከእንጨት ሥራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ኬሚካሎችና ማቴሪያሎች ንግድ ነክ ተግባራትን ያከናውናል፤ 9. Undertake business-related activities as regards chemicals and other materials having to do with forestry development and wood works thereof; 10. አዋጭነቱን በማረጋገጥ ደንና የዱን እንስሳትን ልማት መሠረት ያደረገ የኢኮቱሪዝም ሥራዎችን ያካሂዳል፤ 10. Carry out eco-tourism activities on the basis of forestry and wild animals development by ascertaining the feasibility of such activities thereof; 11. በደንና በደን ውጤቶች ላይ በሚደረግ ምርምርና ጥናት ይሳተፋል፣ ይደግፋል፤ 11. Participate in and support the study and research activities to be conducted on forestry and forest products; 12. በደን ልማት ሥራዎች ላይ ለተሠማሩ ወገኖች የማማከርና የሥልጠና አገልግሎት ይሰጣል፤ 12. Render advisory and training services to those engaging themselves in forestry development activities; 13. ማሽነሪዎችን፣ ተሽከርካሪዎችንና ሌሎች ንብረቶችን እንደአስፈላጊነቱ ያከራያል፡ይከራያል፤ 13. Lease out or obtain by rent machineries, vehicles and other properties, as deemed necessary; 14. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ብድሮችን በማጥናት ለክልሉ መንግስት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤ 14. Own property, enter into contracts, as well as sue and be sued in its own name, study and submit medium and long term loans to the Regional Government and implement same up on approval. 15. ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉትንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት ያከናውናል። 15. Perform such activities as are necessary for the attainment of its objectives and other related ones thereof. www.abyssinialaw.com ገፅ-9- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -9 7. ድርጅታዊ አቋም 7. Organizational Structure ኢንተርፕራይዙ በዚህ ደንብ መሠረት የሚከተሉት አካላት ይኖሩታል፦ The Enterprise shall, pursuant to this regulation , have the following organs: 1. የሥራ አመራር ቦርድ 1. A managing board; 2. በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና 2. A General manager to be appointed by the Head of the Regional Government and, 3. ሌሎች የበታች የሥራ ኃላፊዎችና ለሥራው የሚያስፈልጉ ሠራተኞች ይኖሩታል። 3. Other subordinate managers and staff necessary for the work. ክፍል ሦስት PART THREE ስለ ቦርዱ አወቃቀር፣ ሥልጣን፣ አሠራርና ስለ ሥራ አስኪያጁ STRUCTURE, POWERS, WORKING PROCEDURE OF THE BOARD AND THE MANAGER 8. ስለ ቦርዱ አመሰራረትና የአባላት ጥንቅር 8. Establishment and Composition of Board’s Membership 1. የኢንተርፕራይዙን ሥራዎች በበላይነት የሚመራና የሚያስተባብር የሥራ አመራር ቦርድ ከዚህ በኋላ “ቦርዱ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል። 1. A managing Board /hereinafter referred to as the “Board”/ that supervises over and coordinates activities of the Enterprise is hereby established under this regulation. 2. የቦርዱ ተጠሪነት ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይሆናል። 2. The accountability of the board shall be to the Head of the Regional Government. 3. የቦርዱ አባላት በቢሮው አቅራቢነት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይሰየማሉ፣ ቁጥራቸውም ከአምስት (5) ያላነሰና ከሰባት (7) የማይበልጥ ይሆናል። 3. Members of the board shall be designated by the Head of the Regional Government upon their presentation by the Bureau; their number may not be less than five (5), but not exceeding www.abyssinialaw.com ገፅ-10- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -10 seven (7). 4. ቦርዱ የራሱ ሰብሳቢና ፀሐፊ ይኖሩታል። 4. The board shall have its own chair person and secretary. 5. የቦርዱ የአገልግለት ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል። 5. The term of office of the board shall be five years. 6. የቦርዱ አባላት አበል በኢንተርፕራይዙ ተጠንቶ በቢሮው የሚወሰን ይሆናል። 6. The allowance of the board members shall be studied by the Enterprise and determined by the Bureau. 9. ስለ ቦርዱ ሥልጣንና ተግባር 9. Powers and Duties of the Board ቦርዱ በዚህ ደንብ መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፦ The Board shall, pursuant to this regulation, have the following powers and duties: 1. የኢንተርፕራይዙን ሥራ አስኪያጅ በመምረጥ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቅርቦ ያሻማል፣ 1. Nominate manager of the Enterprise and submit him/her to the Head of the Regional Government to be so appointed ; 2. ኢንተርፕራይዙ የሚመራበትን አጠቃላይ ፖሊሲ በቢሮው አማካኝነት ለርዕሰ መስተዳድሩ አቅርቦ ያፀድቃል፣ በተግባር ላይ መዋሉንም ይከታተላል፣ 2. Submit the general policy in which the Enterprise is to be managed to the Head of the Regional Government through the Bureau as well as cause the approval; follow up the implementation of same; 3. የኢንተርፕራይዙን ዕቅድና በጀት መርምሮ ያፀድቃል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፣ 3. Review and approve the plan and budget of the enterprise; monitor its implementation thereof; 4. ኢንተርፕራይዙ በሰው ኃይል፣ በመሳሪያና በሥራ አመራር የሚጠናከርበትን መንገድ ይቀይሳል፤ 4. Devise a way through which the enterprise may be strengthened in terms of human resource, material and management thereof; 5. የኢንተርፕራይዙ ሃብትና ንብረት በአግባቡ መያዙንና መጠበቁን 5. Follow up that the resource and property of the enterprise is properly handled and protected thereof; ensure that its www.abyssinialaw.com ገፅ-11- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -11 ይከታተላል፣ የገንዘብና የሰው ኃይል አጠቃቀሙም በዚህ ደንብ መሠረት ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፤ utilization of finance and human resource is compatible with the objectives for which it was established pursuant to this regulation; 6. የራሱ ውስጣዊ የሥነ-ሥርዓት መመሪያ ቀርፆ ተግባራዊ ያደርጋል፤ 6. Formulate and implement its own guide lines of internal working procedure. 7. ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወቅታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን ያቀርባል። 7. Submit periodic activity reports to the head of the Regional Government. 10. ስለ ቦርዱ የስብሰባ ጊዜና የውሣኔ አሰጣጥ ስነሥርዓት 10. Meeting Time and Decision Making Procedure of the Board 1. ቦርዱ በ3 ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል፣ 1. The Board shall convene regular meeting once in three months; provided that wherever it finds it necessary, it may hold an extraordinary meeting at any time; 2. ከቦርዱ አባላት ሁለት ሦስተኛው በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ ይሆናል፣ 2. There shall be a quorum where two third of the members of the board show up at the meeting; 3. የቦርዱ ውሣኔዎች በድምፅ ብልጫ ያልፋሉ። ሆኖም ድምፁ እኩል በኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል። 3. Decisions of the board shall be passed through majority vote; provided, however, that, in case of a tie, the chair person shall have a casting vote. 11. የሥራ አስኪያጁ ሥልጣንና ተግባር 11. Powers and Duties of the Manager 1. የኢንተርፕራይዙ ሥራ አስኪያጅ በዚህ ደንብ አንቀጽ 6 ሥር ለኢንተርፕራይዙ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች የማከናወን ሥልጣን ይኖረዋል። 1. The manager of the Enterprise shall have powers to perform duties and responsibilities vested to the enterprise under Art.6 of this regulation hereof. www.abyssinialaw.com ገፅ-12- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -12 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ሥር የሰፈረው አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ሥራ አስኪያጁ ከዚህ በታች የተመለከቱት ልዩ ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፦ 2. Without prejudice to the general provision of sub. Art. 1 of this article hereof, the manager shall have the special powers and duties specified herein below: ሀ) የኢንተርፕራይዙን ሥራዎች ይመራል፣ ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፤ A. Direct, administer and supervise over the activities of the enterprise; ለ) የኢንተርፕራይዙን የአጭር የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድ፣ በጀትና የሥራ ፕሮግራም እያዘጋጀ ለቦርዱ ያቀርባል፣ ሲደፀድቅም በተግባር ላይ ያውላል፤ B. Prepare the short, medium and long-term plan, budget and program of the Enterprise, submit same to the board and put into effect upon approval; ሐ) ተጠሪነታቸው ለሥራ አስኪያጁ የሆኑ የኢንተርፕራይዙን የሥራ ኃላፊዎች ቅጥር፣ ምደባና ስንበት በሚመለከት ለቦርዱ አቅርቦ ያስፀድቃል፣ C. Submit to and have appointed by the board the recruitment, assignment and dismissal of the Enterprise’s work heads accountable to him; መ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ (ሐ) ሥር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አግባብነት ባለው ሕግና በኢንተርፕራይዙ የአስተዳደር ደንብ መሠረት ሠራተኞቸን ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፣ ያሳድጋል፣ ያሰናብታል፣ D. Without prejudice to the provision of this sub. Art. (C) hereof, recruit, administer, promote and dismiss employees, pursuant to pertinent law and administrative rules of the enterprise; www.abyssinialaw.com ገፅ-13- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -13 ሠ) የኢንተርፕራይዙን ጽ/ቤት ያደራጃል፣ የሥራ መዋቅር፣ የሠራተኞችን ደመወዝና አበል እያዘጋጀ ለቦርዱ ያቀርባል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ E. Organize the office of the enterprise, prepare its working structure, salary and allowance of employees, submit same to the board and follow up its implementation up on approval; ረ) የኢንተርፕራይዙን የባንክ ሂሣብ ይከፍታል፣ ያንቀሳቅሳል፤ F. Open and operate the bank account of the enterprise; ሰ) ኢንተርፕራይዙ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል፣ በሥራ ላይ መዋሉንም ይቆጣጠራል፤ G. Cause the withdrawal of money in accordance with budget appropriated to the Enterprise and working program and thereby supervise over its implementation thereof; ሸ) የቦርዱን መመሪያዎችና ውሣኔዎች ይፈፅማል፣ ያስፈፅማል፤ H. Implement and cause the implementation of the directives and decisions of the board. ቀ) ኢንተርፕራይዙ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚገኘው ገቢ በአግባቡ መሰብሰቡን ይቆጣጠራል፤ I. Supervise that the income to be obtained from the services provided by the enterprise is properly collected thereof; በ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉት ግንኙነቶች ሁሉ ኢንተርፕራይዙን ይወክላል፤ J. Represent the Enterprise in all relations with the third parties; ተ) የሥራ አፈፃፀምና የፋይናንስ አጠቃቀም ዘገባዎችን እያዘጋጀ በየሩብ ዓመቱ ለቦርዱ ያቀርባል፤ K. Prepare and submit to the board quarterly performance and financial reports on quarterly base; ቸ) የቦርዱ ፀሐፊ በመሆን ያገለግላል L. Act as a secretary of the board; ነ) በቦርዱ የሚሰጡትን ሌች ተግባራት ያከናውናል። M. Perform such other duties as may be assigned to him. www.abyssinialaw.com ገፅ-14- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -14 ክፍል አራት PART FOUR ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች MISCELLANEOUS PROVISIONS 12. የኢንተርፕራይዙ ሠራተኞች ቅጥርና አስተዳደር 12. Recruitment and Administration of the Enterprise’s Employees 1. የኢንተርፕራይዙ ሠራተኞች ቅጥርና አስተዳደር በሃገሪቱ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሕግ መሠረት የሚገዛ ይሆናል። 1. The recruitment and administration of employees of the Enterprise shall be governed by the country’s labor laws. 2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ሥር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ኢንተርፕራይዙ እንደአስፈላጊነቱ የራሱን የሠራተኛ መተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል። 2. Without prejudice to the provision stipulated under sub.art.1 of this article hereof, the Enterprise shall prepare and put into effect administrative regulation of its own, as deemed necessary. 13. ስለኢንተርፕራይዙ የበጀት ምንጮች እና የበጀት ዓመት 13. Budgetary Sources and Fiscal Year of the Enterprise 1. የኢንተርፕራይዙ በጀት የሚገኘው ከሚከተሉት የፋይናንስ ምንጮች ይሆናል። 1. The budget of the Enterprise shall be obtained from the following financial sources: ሀ) ከክልሉ መንግስት የሚገኝ የመቋቋሚያ ካፒታልና ብድር ፈንድ፣ A. Initial capital and loan fund to be generated from the Regional Government; ለ) ኢንተርፕራይዙ የሚሰበስባው የአገልግሎትና ሽያጭ ክፍያዎች፣ B. Service and sales charges to be collected by the Enterprise; ሐ) ከፋይናንስ ተቋማት ወይም ከሌሎች ድርጅቶች የሚገኝ የዓይነትም ሆነ የጥሬ ገንዘብ ስጦታ ወይም ድጋፍና C. Donations in kind or cash or support which the Enterprise may obtain from financial institutions or other organizations and; መ) ከሌሎች ምንጮች D. Other sources. www.abyssinialaw.com ገፅ-15- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -15 2. የኢንተርፕራይዙ የበጀት ዓመት የክልሉ መንግስት የበጀት ዓመት ይሆናል። 2. The fiscal year of the Enterprise shall be that of the Regional State. 14. ስለ የሂሣብ መዛግብት 14. Books of Account 1. ኢንተርፕራይዙ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል፤ 1. The Enterprise shall keep complete and accurate books of account. 2. አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ቦርዱ የኢንተርፕራይዙን የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች አያያዝ በተመለከተ ተቀባይነት ያላቸው የሂሣብ አሠራሮች በሥራ ላይ እንዲውሉ ሊያደርግ ይችላል። 2. Wherever it finds it necessary, the board may cause the operation of an acceptable accounting system as of regards the maintenance of books of account and finance related documents of the Enterprise. 15. ስለ ሂሣብ ምርመራ 15. Auditing ኢንተርፕራይዙ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብም ሆነ ንብረት ነክ ሰነዶች በክልሉ ዋናው ኦዲተር ወይም ቦርዱ በሚሰይማቸው የውጭ ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ። The Books of account and financial as well as property related documents of the Enterprise shall be audited yearly by the office of the Auditor General of the Regional State or by External Auditors to be assigned by the board. 16. መብትና ግዴታን ስለማስተላለፍ 16. Transfer of Rights and Obligations የመንግስት ደኖችንና ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በክልሉ መንግስት አማካኝነት ለቢሮውም ሆነ ለሌሎች አካላት ተሰጥተው የነበሩ መብቶችና ግዴታዎች የተቆጣጣሪነት ጠባይ ያላቸው ካልሆኑ በስተቀር በዚህ ደንብ አማካኝነት ወደ ኢንተርፕራይዙ ተላልፈዋል። The rights and obligations vested in the Bureau and other organs by the Regional State with regard to the government forests and projects are, with the exception of those having regulatory characters, hereby transferred to the enterprise as per this regulation hereof. www.abyssinialaw.com ገፅ-16- ዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም Zikre-Hig Gazette No.1 13th Day of October, 2009, page -16 17. ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ህጐች 17. Inapplicable Laws ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን ማናቸውም የክልሉ ደንብ፣ መመሪያ ወይም የተለመደ አሠራር በዚህ ደንብ ውስጥ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖርውም። Any Regional regulation, directive or customary practice, inconsistent with this regulation, may not apply to matters not included in this regulation therein. 18. መመሪያ የማውጣት ስልጣን 18. Power to Issue Directives ይህንን ደንብ በተሟላ ሁኔታ በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉትን መመሪያዎች ቦርዱ ያወጣል። The board may issue directives necessary for the full implementation of this regulation. 19. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ 19. Effective Date ይህ ደንብ በክልሉ መንግስት ዝክረ ሕግ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል። This regulation shall come into force as of the date of its publication on the Zidre Hig Gazett of the Regional State. ባህር ዳር ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም አያሌው ጐበዜ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር Done at BahirDar This 13 th day of Oct, 2009 Ayalew Gobezie Head of Government of the Amhara National Regional State www.abyssinialaw.com

Forestry Enterprise Establishment, Council of Regional Government Regulation No 70/2009 · Nelum